ከቦሌ ቀጥሎ ትልቁ ተርሚናል፤ የባሕር ዳር የደጃዝማች በላይ ዘለቀ ኤርፖርት
*******************
በኢትዮጵያ የእድገት ጉዞ ውስጥ ልዩ ትኩረት ከተሰጣቸው መሠረታዊ የልማት ዘርፎች መካከል የአቪዬሽን ኢንዱስትሪው አንዱና ዋናው ነው።
ለዚህ ዘርፍ በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ምክንያት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሀገሪቱ በርካታ አወንታዊ ለውጦችና የእድገት ማሳያዎች እየታዩ ይገኛሉ።
በተለይም የሀገር ውስጥ የመዳረሻ ኤርፖርቶች ቁጥር እየጨመረና የመሰረተ ልማት አቅማቸው እየጎለበተ መምጣቱ፣ የከተሞችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ከመሆኑም በላይ፤ ከተሞች ማግኘትና መልማት በሚገባቸው ልክ እንዲያድጉ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።
በአማራ ክልል ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተከናወኑ የመሰረተ ልማት ስራዎች የዚሁ ትልቅ ጉዞ ማሳያ ናቸው።
በቅርቡ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት የጀመረውን የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያን ጨምሮ፣ በአሁኑ ወቅት የባሕር ዳር የደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት አዲስ ዘመናዊ ተርሚናል ግንባታ ተጠናቆ ለእንግዶች መቀበያነት ዝግጁ ሆኗል።
ይህ ተርሚናል ቀደም ሲል የነበረውን ጠበብ ያለና ምቹ ያልሆነ አሰራር ሙሉ በሙሉ በመቀየር፣ ዘመኑን በዋጀ መልኩ በሰፊ እና በዘመናዊ የሕንፃ ጥበብ የተገነባ ነው።
ይህ አዲስ ተርሚናል ከአዲስ አበባው ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቀጥሎ ሁለተኛው ትልቅ የእንግዶች መቀበያ መሆን የሚያስችለውን አቅም ይዟል።
ይህም የባሕር ዳር ከተማን ውበት፣ ለምለምነትና የቱሪዝም መስህብነት ለሚመጡ መንገደኞች በግልጽ የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ፣ ህብረተሰቡ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን ተመልክቶ በተግባር ተጠቃሚ እንዲሆን ያደርጋል።
በአጠቃላይ እነዚህ መሰል የኤርፖርት መሰረተ ልማት ስራዎች በአንድ አካባቢ ብቻ የተወሰኑ ሳይሆኑ በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች በስፋት እየተከናወኑ የሚገኙ ናቸው። ይህም የከተሞችን ውበትና ተደራሽነት ከመጨመር ባሻገር፣ የኢትዮጵያ የነገ እድገትና የብልፅግና ጉዞ በተስተካከለና በጥሩ መስመር ላይ እንደሚገኝ በግልጽ የሚያሳይ አዎንታዊ ማሳያ ነው።
#ethiopia #bahirdarairport #ethiopianaviation #bahirdar #ethiopianairlines

2 months ago