ከ4መቶ በላይ ፌስታል የሚያመርቱ ተቋማት ላይ ክትትልና ቁጥጥር ማድረጉን የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ተናገረ
ባለስልጣኑ የፕላስቲክ ምርቶች ለገበያ እንዳይቀርቡና ምርቱም እንዲቆም የሚያደርገዉ ህግ ወደ ስራ መግባቱን ተከትሎ ቁጥጥር እያደረጉ እገኛለሁ ብሏል።
በዚህም መሠረት በተጠናቀቀው በጀት አመት ከረጢት ስራ ላይ እንዳይውል ለማድረግ በተሰራው ስራ 4መቶ 88 ፌስታል የሚያመርቱ ተቋማት ላይ ክትትልና ቁጥጥር ተደርጓል ተብሏል።
አሁንም በርካታ የምርት ክምችቶች በቁጥጥር ስር እየዋሉ እንደሚገኝ የገልፁት የባለስልጣኑ ዋና አማካሪ አቶ አዱኛ ወንድሙ ባለስልጣኑ በደረሰበት ልክ ክትትል እያደረገ ቢሆንም ህብረተሰቡ ስለፌስታል ያለውን ግንዛቤ መቀየር ካልተቀየሩ ምርቱን በቀላሉ ማስቆም እንዳልተቻለ ተናግረዋል።
አምራች ተቋማቱ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እና ወደ ሌሎች ተኪ ምርቶች እንዲሰማሩ በማድረግ ያላሻሻሉት ላይ እስከማሸግ የደረሰ እርምጃ መውሰድ እንደተቻለም አያይዙዉ ገልፀዋል።
በበጀት አመቱ ከብክለት ጋር በተያያዘ ከ17ሺ 1መቶ በላይ ተቋማት ላይ ባደረገው ክትትልና ቁጥጥር መደረጉ ተነግሯል።
ህግ ተላልፈው የተገኙ 3ሺ 3መቶ 18 ተቋማት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷልም ተብሏል።
ቁምነገር አየለ

13 hours ago