በ21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለት ሜዳሊያዎችን አገኘች
በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት ዩጂን ከተማ በሚገኘው ሄይዋርድ ፊልድ ስታዲየም በተጀመረው 21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች (U20) የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በመጀመሪያው ቀን ሁለት ሜዳሊያዎችን አስመዝግባለች።
በሴቶች 5000 ሜትር ፍጻሜ ሽቶ ጉሚ 15 ደቂቃ ከ07.91 ሰከንድ በሆነ ሰዓት ርቀቱን በማጠናቀቅ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳሊያ አግኝታለች። የኡጋንዳዋ ቻሪቲ ቼሮፕ የወርቅ ሜዳሊያውን ስታሸንፍ፣ የኬንያዋ ጆይስሊን ችፕኬሞይ ደግሞ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች።
በወንዶች 5000 ሜትር ፍጻሜ ደግሞ ዳምጠው ከበደ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ የነሐስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አበርክቷል። በዚህ ውድድር ኬንያውያን ፍራንክሊን ኪቤት እና ነህሚያ ኪፕንጌኖ በቅደም ተከተል አንደኛና ሁለተኛ ደረጃዎችን ይዘው አጠናቀዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ የሻምፒዮናውን የመጀመሪያ ቀን በአንድ የብር እና በአንድ የነሐስ ሜዳሊያ በድምሩ ሁለት ሜዳሊያዎች በማግኘት ጀምራለች።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #ethiopianathletics #worldathletics #u20athletics #sports

10 hours ago