Logo
EBC
በቅንነትና በትጋት ለሚያገለግል አመራር ህዝቡ ጠንካራ ጋሻና ደጋፊ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
***************************

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባለፉት አምስት ዓመታት የተመዘገቡ ድንቅ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በማረጋገጥ፣ በቀጣዮቹ ዓመታት የሚጠበቁት የኢኮኖሚና የፖለቲካ እመርታዎች ለአመራሩ እንቅልፍ የሚነሱ ከባድ ኃላፊነቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዝብ አደራ ከምረጡኝ ዘመቻው በላይ እጅግ የሚከብድ መሆኑን በንግግራቸው አጽንዖት ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ አደራ ሲሰጥ የጥይት ድምፅ፣ ግርግርና ማስፈራራት እንዳላገደው ሁሉ፤ ይህ አደራ በአግባቡ ካልተያዘ ህዝቡ መብቱን ለማስከበር ወደኋላ እንደማይል አስገንዝበዋል።

አመራሩ በታመነበት ልክ በቅንነትና በትጋት ሲመላለስ ህዝቡ እንደሚጠብቀው፣ እንደሚከላከልለት እና ለስኬቱም ጠንካራ ጋሻና ደጋፊ እንደሚሆነው አብራርተዋል።

በተቃራኒው ግን አመራሩ አደራውን ሲያጎድልና ከህዝብ ፍላጎት ሲያፈነግጥ የሰጠውን አደራ የመንጠቅና መብቱን የማስከበር ሙሉ አቅምና ታሪክ እንዳለው በግልጽ አመልክተዋል።

በቀጣዮቹ ዓመታት በሀገሪቱ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ዘርፍ የሚፈለገውን ትልቅ እመርታ ለማምጣት መንግስት በከፍተኛ ቁርጠኝነት እንደሚሰራ እና ህዝቡ የጣለበትን ከባድ አደራ ለመወጣት ሌት ተቀን እንደሚተጋ አረጋግጠዋል።

በቢታኒያ ሲሳይ
#ethiopia #leadership #publictrust #abiyahmed #politics

4 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.