Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በ3 ወራት ውስጥ 1 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ደንበኞችን ማፍራቱን አስታወቀ፡፡ በኢትዮጵያ 2ተኛው የቴሌኮም አቅራቢ የሆነው ሳፋሪ ኮም የደንበኞቹ ቁጥር 14.7 ሚሊዮን መድረሱን ገለፀ፡፡ ይህም በኢትዮጵያ ውስጥ የጀመረውን ስራ በማርች ወር 2027(እ.ኤ.አ) ወደትርፋማነት ለማሸጋገር የወጠነውን እቅድ እንደሚያጠናክርለት አስረድቷል፡፡

ሳፋሪኮም የዘንድሮ በጀት አመት አፈፃፀሙን በተመለከተ ባወጣው ሪፖርት በሩብ አመቱ ወይንም ባለፉት 3 ወራት ውስጥ ከ1 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ደንበኞችን ማግኘቱን ጠቁሞ ከኬንያ ውጭ በከፍተኛ ሁኔታ አገልግሎቱን እያስፋፋ ያለው በኢትዮጵያ መሆኑን አስታውቋል፡፡ ይህ ውጤትም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እንቅስቃሴ ወደዘላቂነት ያለው እድገት እየሄደ መሆኑን እንደሚያሳይ ገልጿል፡፡

ሳፋሪኮም እንዳለው ባለፈው በጀት አመት በኢትዮጵያ ያሉት ደንበኞቹ ቁጥር 10.06 ሚሊዮን የነበረ ሲሆን ዘንድሮ 14.7 ሚሊዮን መድረሳቸው የ46.1 አንድ ጭማሪ መታየቱን ያመላክታል፡፡ በዘርፉ በመንግስት ባለቤትነት የሚተዳደረው ተቋም ትልቅ ድርሻ ያለው ቢሆንም የታየው እድገት ግን ተስፋ ሰጪ መሆኑንም ጠቅሷል፡፡

8 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.