ይሄን ምስኪን ምን አድርግ ነው የምትሉት?
#ethiopia | የናቲ ገጠመኝ በግለሰብ ደረጃ የተፈጸመ ቅጥ አልባ ድርጊት ብቻ ሳይሆን በአሁኑ ወቅት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ "እይታን" ለመቃረም ሲባል የሚደረግ የዘመኑ ልክፍት ነው።
ይህ ድርጊት ከቀልድነት አልፎ በሰዎች ሰላማዊ ህይወት ላይ የሚፈጸም ጥቃት ነው!
በመሠረቱ ፕራንክ የሚሉት ነገር ለዛ ቢስ ጨዋታ ነው ነገር ግን ፤ ይሁን ይደረግ ከተባለም (አድራጊውንም ሆነ ተደራጊውን) መጨረሻው የማያሳቅቅ እና የሰዎችን ስሜት የማይጎዳ መሆን ይገበዋል፤ አሁን አሁን ግን ሰዎችን ማዋከብ፣ ማስደንገጥ እና ስነ-ልቦናዊ ጫና ማድረስ እንደ መዝናኛ እየተቆጠረ ነው።
የናቲ ድንጋጤ እና ፊቱ ላይ ይነበብ የነበረው ጭንቀት ለነሱ "ጥሩ የቲክቶክ ቪዲዮ" ሲሆን፣ ለሱ ግን ትርጉሙ ሌላ ነው።
ሌላው የደንብ ልብስን አላግባብ መጠቀምስ ይቻላል ወይ?
አንደኛው ግለሰብ የፖሊስ ልብስ(የሚመስል) ለብሶ መምጣቱ ድርጊቱን ከስነ-ምግባር ግድፈት አልፎ ከባድ የህግ ጥሰት ያደርገዋል።
ዜጎች በጸጥታ አስከባሪዎች ላይ ሊኖራቸው የሚገባውን እምነት የሚሸረሽር እና የመንግስትን የደንብ ልብስ ለግል የሶሻል ሚዲያ ትርፍ ማዋረድ ነው።
የሰውን ልጅ ሰላም ነስቶ የሚገኝ ላይክ ዋጋው ስንት ነው?
መፍትሄው እና መማር ያለብን እሴት
፣ ከዚህ ሁሉ ጫጫታ እና የሰዎችን ክብር ከሚረግጥ አዝማሚያ ወጥተን ሰውን በማክበር ረገድ እንድናስብ ያስፈልጋል።
ጥበብ ሰውን በማክበር እንጂ ሰውን በማዋረድ ውስጥ የለችም።
የሚዲያ ተጠቃሚውም ቢሆን እንዲህ አይነት ሰብዓዊ ክብርን የሚጋፉ ይዘቶችን ከማበረታታት፣ ከማየት እና ከማጋራት በመቆጠብ ይህንን እኩይ ተግባር ሊያወግዘው ይገባል። ሰውን ማክበር ኋላቀርነት ሳይሆን የስልጣኔ ሁሉ ቁንጮ ነው።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

8 days ago