የቀድሞው የሲዳማ ክልል የፀጥታ ኃላፊ እና የፖሊስ ኮሚሽነር በተመሰረተባቸው ከባድ የወንጀል ክሶች ጥፋተኛ ተብለው በእስራትና በገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ተወሰነ
የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሲዳማ ክልል የቀድሞ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ እና በቀድሞው የፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ሽመልስ ቶማስ ላይ የፍርድ ውሳኔ አስተላልፏል።
ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው በክልሉ ፍትሕ ቢሮ አቃቤ ህግነት የቀረቡትን ክሶች፣ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በጥንቃቄ በማመሳከርና ተከሳሾቹ ጥፋተኛ መሆናቸውን በማረጋገጥ ነው።
እንደ ፍትሕ ቢሮው ማብራሪያ፣ የቀድሞዎቹ የመንግሥት ኃላፊዎች የተከሰሱበትና ጥፋተኛ የተባሉበት ዋና ምክንያት የተሰጣቸውን መንግሥታዊ ሥልጣን አላግባብ በመጠቀም ነው። ኃላፊዎቹ «የሲዳማ ነፃነት ሠራዊት (ሲነሠ)» የተባለ ታጣቂ ቡድን በማደራጀት እና ተደራራቢ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመፈጸማቸው በህግ ፊት እንዲጠየቁ ተደርጓል።
በዚሁ መሠረት ፍርድ ቤቱ ሐምሌ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. በዋለው ችሎት፣ 1ኛ ተከሳሽ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ በ10 ዓመት ከ5 ወር ጽኑ እስራት እና በ4,000 ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ ወስኗል።
በተመሳሳይ መዝገብ የተከሰሱት 2ኛ ተከሳሽ አቶ ሽመልስ ቶማስ ደግሞ በ1 ዓመት ከ6 ወር ጽኑ እስራት እና በ1,000 ብር መቀጮ እንዲቀጡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሰጥቷል።
Seledadotio

11 days ago