Logo
EBC
“በጋና አክራ ከተማ የሚገኘውን ታሪካዊውን የክዋሜ ንክሩማህ መታሰቢያ ፓርክን ጎብኝተናል” - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
*********************

“በጋና አክራ ከተማ የሚገኘውን ታሪካዊውን የክዋሜ ንክሩማህ መታሰቢያ ፓርክን ጎብኝተናል፤ በሐውልታቸው ሥርም የአበባ ጉንጉን አኑረናል” ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ስፍራው የጋና የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት እና የፓን-አፍሪካኒዝም አቀንቃኝ የዶክተር ክዋሜ ንክሩማህ እንዲሁም የባለቤታቸው የፋቲያ ንክሩማህ መካነ መቃብርና ታሪካዊ ሙዚየምን ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል።

ጋናውያን ለአፍሪካ ነፃነትና አንድነት አቀንቃኙ መሪያቸው ግዙፍ ሐውልት መታሰቢያ መገንባታቸው የቀደሙትን ማክበር ለትውልድና ለሀገር ግንባታ ያለውን ሚና ያሳያል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን በማኅበራዊ ትስስር ገጽ ባጋሩት መልዕክት።

ዶ/ር ክዋሜ ንክሩማህ ለጋና ነፃነት ብቻ ሳይሆን፣ ሙሉ አፍሪካ ከቅኝ ግዛት ነፃ እንድትወጣ የነበራቸው ራዕይ ዛሬም ድረስ ለትውልዱ ትልቅ የብርታት ምንጭ ነውም ብለዋል።

በተለይም ከኢትዮጵያ ጋር የነበራቸው ጥብቅ ወዳጅነት እና ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የአሁኑ አፍሪካ ኅብረት) መመስረት ያበረከቱት አስተዋጽኦ ሁልጊዜም በክብር የሚታወስ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

15 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.