ቢል ጌትስ የአፍሪካ መሪዎችን መከሩ
*የአፍሪካ መሪዎች በሰው ኃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ መክረዋል።
#ethiopia | የማይክሮሶፍት መስራች ቢል ጌትስ የአፍሪካ መሪዎች በሰው ኃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ላይ በአስቸኳይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ መክረዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለልማት የሚሰጡ የእርዳታ በጀቶች እየቀነሱ መምጣታቸውን የጠቀሱት ቢል ጌትስ ይህ በአፍሪካ መንግስታት ላይ ከፍተኛ የፋይናንስ ጫና እየፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።
የአህጉሪቱ ትልቁ ሀብት ወጣቶች መሆናቸውን የገለጹት ጌትስ በጤና፣ በትምህርት እና በፈጠራ ስራዎች ላይ ኢንቨስት ማድረግ የወጣቶችን ቁጥር ወደ ኢኮኖሚ መቀየር ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ወይም ሰው ሰራሽ አስተውሎት የአፍሪካን ትልልቅ ችግሮች ለመፍታት ትልቅ እምቅ አቅም እንዳለው ጠቁመዋል።
በተለይም በጤና በትምህርት እና በግብርና ዘርፎች ላይ የሰው ኃይልን በማገዝ ምርታማነትን ለመጨመር እና የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚረዳ ገልጸዋል።
ቢል ጌትስ አክለውም ምንም እንኳን ሀገራትና ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ ቢያደርጉም የረጅም ጊዜ ዘላቂ እድገት የሚመጣው ጠንካራ የሀገር ውስጥ ተቋማት በመገንባት እና በራስ አቅም ላይ በመተማመን መሆኑን አሳስበዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #billgatesafricanleaders #investpeopletechnology #microsoftdonation

15 days ago