Logo
SeledaPost
በሀዋሳ ከተማ 120 ሊትር ነዳጅ የሚይዝ ህገ-ወጥ ታንከር በባጃጁ ላይ አስገጥሞ ሲንቀሳቀስ የነበረው ሹፌር ተያዘ
 
​በሀዋሳ ከተማ በባለ ሦስት እግር (ባጃጅ) ተሽከርካሪ ላይ ህገ-ወጥ ተጨማሪ ታንከር በመግጠም ነዳጅ ሲቀዳ የነበረው ሹፌር በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን የከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።ግለሰቡ  በባለ ሦስት እግር (ባጃጅ) ተሽከርካሪ ውስጥ የወንበር ቅርጽ ያለው ህገ-ወጥ ታንከር አስገጥሞ መገኘቱ ተገልጿል።
 
​የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምክትል አዛዥና የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ኃላፊ ኮማንደር አብስራ አመሎ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለፁት ግለሰቡ  በተሰራው ህገ-ወጥ ታንከር ውስጥ 120 ሊትር ነዳጅ የተገኘ ሲሆን ባጃጁ በመደበኛ ሁኔታ መያዝ የሚችለው 8 ሊትር ብቻ  ነዉ።
 
​በዚህም  የባጃጅ ሹፌሩን ጨምሮ በጋራ ሲሰሩ የነበሩ የነዳጅ ማደያው ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል።ፖሊስ ከንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ጋር በመተባበር ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ገልጾ የክስ መዝገብ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ አስረድቷል። መሰል ህገ-ወጥ የነዳጅ ዝውውርና የማከማቸት ተግባር በሀገር ኢኮኖሚ እና በህብረተሰብ ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል በመሆኑ  በድርጊቱ ላይ በሚሳተፉ አካላት ላይ የሚወሰደው ህጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮማንደር አብስራ አመሎ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
 
በሳምራዊት ስዩም

Seledadotio
Seledadotio
16 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.