Logo
FastMereja
ኮካ ኮላ ያዘጋጀው ታላቁ የዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በስካይላይት ሆቴል ሊደገም 2 ቀናት ብቻ ቀሩት! 🏆

በመላው ዓለም በከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቀው የ23ኛው የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ላይ ደርሰናል። በመክፈቻው ምሽት በስካይላይት ሆቴል ያሳለፍነውን ያንን የማይረሳና ደማቅ ጊዜ፣ አሁን በታላቁ የፍፃሜ ምሽት በደመቀ ሁኔታ ለመድገም ሰዓታት እየተቆጠሩ ነው!

ኮካ ኮላ ከዲኤስቲቪ ጋር በመተባበር ለዚህ ታሪካዊ ምሽት ልዩና አስደናቂ ዝግጅቶችን አሰናድቷል፡

⚽ በጉጉት የሚጠበቀውን የስፔን እና የአርጀንቲናን እጅግ አጓጊ የዋንጫ ጨዋታ፣ በዲኤስቲቪ እጅግ ጥራት ባለው ግዙፍ ስክሪን በጋራ እንመለከታለን!

🎶 ምሽቱን ይበልጥ የማይረሳ የሚያደርጉት ተወዳጆቹ ድምፃውያን ፀደኒያ ገ/ማርቆስ፣ አዲስ ለገሰ እና ልዑል ሲሳይ ድንቅ የሙዚቃ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ።

🎮 በስፍራው የተዘጋጁ ልዩ ልዩ የቪዲዮ ጌሞች እና አስደሳች የውድድር መድረኮች።

🍽️ የምሽቱን ድባብ ፍፁም የሚያደርግ እጅግ ጣፋጭ የራት ግብዣ።

አዘጋጅ፦ ኮካ ኮላ ከዲኤስቲቪ (DStv) ጋር በመተባበር

🚨 ማሳሰቢያ፦ ይህ ፕሮግራም ጥሪ የተደረገላቸው ለክብር እንግዶች ብቻ የተዘጋጀ ነው።
#fifaworldcup2026 #cocacola #feelitall #ccbaethiopia #worldcupfinal #spainvsargentina #cocacolaethiopia #dstvethiopia

20 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.