መንግሥት በፈቀደው የ4 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት የአላይድ ጎልድ አክሲዮን ዋጋ ጨመረ
#ethiopia | የኢትዮጵያ መንግሥት አላይድ ጎልድ ለቻይናው ዚጂን ማይኒንግ ሊያደርገው ባቀደው የ4 ቢሊዮን ዶላር የሽያጭ ስምምነት ላይ ይሁንታውን መስጠቱን ተከትሎ፣ የኩባንያው አክሲዮን ዋጋ የ1 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።
ካፒታል ጋዜጣ ምንጮቹን ጠቅሶ እሁድ ዕለት ባወጣው ዘገባ መሠረት የአገሪቱ ተቆጣጣሪ አካላት ባለፈው ሳምንት ስምምነቱን ያፀደቁት ሲሆን ሁለቱ ወገኖችም የሽያጭ ውሉን እስከዚህ ወር መጨረሻ ድረስ ሙሉ በሙሉ ያጠናቅቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዚጂን ማይኒንግ በአጠቃላይ 5.5 ቢሊዮን የካናዳ ዶላር (4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር) በሆነ ዋጋ አላይድ ጎልድን ለመግዛት በጥር ወር ላይ መስማማቱ ይታወሳል።
በአሁኑ ወቅት የማዕድን ማውጫ ፋብሪካው ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በቅርቡ በይፋ ለመመረቅ በመጠባበቅ ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህ ተስፋ ሰጪ እመርታም ለኩባንያው ያለው ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር ማድረጉ ተገልጿል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

21 days ago