Logo
FastMereja
ብረሽድ ባይ ቤቲ የውበት ማሰልጠኛ ተቋም ከ400 በላይ ሰልጣኞችን አስመረቀ!
#fastmereja :- በውበትና ስልጠና ዘርፍ ለ11 ዓመታት ሲያገለግል የቆየው ብረሽድ ባይ ቤቲ (BBMI) የውበት ማሰልጠኛ ተቋም፣ ለሰባተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ከ400 በላይ ተማሪዎች በዛሬዉ እለት በኤልያና ሆቴል አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በሜካፕ፣ በሰው ሰራሽ አይላሽ አሰራር፣ በጥፍር ውበት፣ በኦምብሬ (የፀጉርና ጥፍር ቀለም ቅልቅል) እና በፌሻል ስልጠና ዘርፎች የሰለጠኑ ሲሆን፣ ስልጠናው በዘርፉ ያለውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎት ከመሙላት ባለፈ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጥርመሆኑ ተገልጿል።

የተቋሙ መስራችና ባለቤት ወ/ሮ ቤተልሄም እስክንድር እንደገለጹት፣ ተመራቂዎቹ በቀጥታ ወደ ሥራ እንዲገቡ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር እየተሠራ እንደሚገኝ ገልፀዉ ተቋሙም በመጀመሪያ ደረጃ የራሱን ድርጅት ሠራተኞች የሚቀጥረው ከራሱ ተማሪዎች መካከል መሆኑን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የራሳቸውን ሥራ መፍጠር ለሚፈልጉ ሰልጣኞች ከተመረጡ ባንኮች ኦና የብድር ተቋማት ጋር በመተባበር የብድር ሁኔታዎች መመቻቸታቸውም ነዉ የተገለፀዉ።

እንዲሁም ተማሪዎቹ ራሳቸውን እና ምርታቸውን ማስተዋወቅ እንዲችሉ ለማገዝም የዲጂታል ማርኬቲንግ፣ ቪዲዮግራፊ፣ ፎቶግራፊ እና የሕይወት ክህሎት ስልጠናዎች በነጻ ተጨማሪ ኮርስ ተደርገው ተሰጥተዋቸዋል።

ተቋሙ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት አንጻር ከመንግሥት አካላት ጋር በመተባበር አቅም ለሌላቸው ሴቶች እና መስማት ለተሳናቸው እህቶች ሙሉ በሙሉ በነጻ ስልጠና መስጠቱን እና ወደፊትም መስጠቱን እንደሚቀጥል ተገልጿል።

በቀጣይም በተለያዩ ምክንያት ከቤት መውጣት ለማይችሉ እናቶችና እህቶች ምቹ የሆነ የቤት ለቤት የኦንላይን (Online) ስልጠና ለመጀመር ዝግጅት መጠናቀቁን ጨምረው አስታውቀዋል።

21 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.