የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት 100ኛ ዓመቱን እያከበረ ነው!
#fastmereja I የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) የ100ኛ ዓመት የምሥረታ በዓሉን ባከበረበት መድረክ፣ ተቋሙ የሕዝብ ጤናን ለመጠበቅ የመንግስትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ገለጹ። በበዓሉ አከባበር ላይ የተቋሙ አዲስ ብራንድ ይፋ የተደረገ ሲሆን ለቀድሞ አመራሮችና ተመራማሪዎችም እውቅና ተሰጥቷል።
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ለኢንስቲትዩቱ ሰራተኞች ላለፉት መቶ ዓመታት ላሳዩት ትጋትና ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል። መንግስት የሀገር ኢኮኖሚን ለመገንባት የህዝብ ጤና ዋነኛው መሰረት መሆኑን እንደሚረዳ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፣ ለዚህም ሲባል የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን የመሰሉ ተቋማትን የመደገፍና የማጠናከር ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው፣ ዛሬ የሚከበረው የአንድ ተቋም 100ኛ ዓመት ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ዘርፍ የተጓዘበትን የዕድገት ጉዞ መሆኑን ገልጸዋል። ተቋሙ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት በወረርሽኝ ልየታ፣ ክትትልና ምላሽ አሰጣጥ ላይ ያስመዘገባቸውን ስኬቶች ያነሱት ሚኒስትሯ፣ መንግስት የጤና ተቋማትን በማስፋፋትና የጤና መድህን አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝና ሚኒስቴሩ ለኢንስቲትዩቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ይህ መድረክ ለቀድሞ አመራሮች፣ ተመራማሪዎች እና ሰራተኞች እውቅና ለመስጠትና ለህብረተሰቡ የተገባውን ቃል ለመደገፍ የተዘጋጀ መሆኑን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሃይሉ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ተቋሙ 40 የሪፈራል ላቦራቶሪዎችን ማቋቋሙንና በክልሎች ድንገተኛ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከያ ማዕከላትን በመገንባት ወረርሽኝን የመቆጣጠር ሥራውን በግንባር ቀደምትነት እየመራ እንደሚገኝ ጠቅሰው፣ ተቋሙ የአፍሪካ የህብረተሰብ ጤና የልህቀት ማዕከል ለመሆን በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን አስታውቀዋል።
#ጤና

21 days ago