አምባሳደሩ ጀኔራሉን እንዳያገኙ ተከለከሉ ‼️
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በትናንትናው የመቀሌ ጉዟቸው ለውይይት ቀጥረዋቸው የነበሩትን አመራሮች ሳያገኙ መመለሳቸውን ተሰምቷል፡፡
አምባሳደሩ በህወሓት እና በፌደራል መንግሥት የተፈጠረውን ውጥርት ለማርገብ፣ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በቻርተር አውሮፕላን ልዑካቸውን አስክትለው ወደ መቀሌ ተጉዘዋል፡፡
ማሲንጋ ወደ መቀሌ ያቀኑትን፣ በዋናነት የህወሓቱን ሊቀመንብረ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤልን እና ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደን ለማነጋገር ነበር ተብሏል፡፡
ማሲንጋ የተወያዩት ከህወሓቱ ምክትል ሊቀመንብር አማኑኤል አሰፋ እና አምባሳደር አዲስአለም ባሌማ ጋር ነው፡፡
ማሲንጋ መቀሌ ከደረሱ በኋላ የተቀበሏቸውና ለውይይት የተቀመጡት ከእነዚሁ ሁለት አመራሮች ጋር ነው፡፡
በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አፍርሰው ሥልጣን የተቆጣጠሩት፣ የህወሓቱ ሊቀመንብር ደብረጽዮን “መቀሌ ውስጥ የሉም” በሚል ምክንያት ከአምባሳደሩ ጋር አልተገናኙም ተብሏል፡፡
የአሜሪካ ልዑክ የመቀሌ ጉዞ በኃይል ሥልጣናቸውን የተቀሙትን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕረዝዳንት ሌተናል ጀነራል ታደሰን ማግኘት አልቻሉም ተብሏል፡፡
ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ ከአደባባይ እይታ የጠፉት ጀነራል ታደሰ አምባሳደሩን እንዳያገኙ በህወሓት የጸጥታ አመራሮች “የደህንነት ስጋት” በሚል እንደከለከላቸው ተሰምቷል፡፡
አምባሳደሩ ጀነራል ታደሰ ወረደን እንዳያገኙ መከልከ የቀድሞ አለቃቸው ጌታቸው ረዳ በፌስቡክ ገጻቸው ጽፈዋል።
Seledadotio

22 days ago