የግድያ ወንጀል የፈጸሙ 11 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
#ethiopia | ሰኔ 28 ቀን 2018 ዓ/ም በግምት ከለሊቱ 7:00 ሠዓት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ቡልቡላ አቦ መሻገሪያ ድልድይ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው የግድያ ወንጀሉ የተፈፀመው።
በወቅቱ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሠብ ከሳሪስ አቦ ወደ ኮዬ መሄጃ በሚገኝ መንገድ ድልድይ ስር ደረቱ ላይ በስለት ተወግቶ ህይወቱ አልፎ ተገኘ።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የሰው መግደል ምርመራ፣ የክትትልና ኦፕሬሽን ቡድኑ በመቀናጀት የሟችን ማንነት ለማወቅ እና ወንጀል ፈፃሚዎችን ለመለየት ባደረገው ጥረት ወንጀሉ በተፈፀመ 48 ሠዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የሟችን ማንነትና እና ወንጀሉን ፈፅመዋል ያላቸውን እንዳለ ተሰማ፣ ኤርሚያስ አሰፋ፣ ያብስራ እንዳለ፣ ዘካሪያስ ለማ፣ ናትናኤል ግርማ፣ ተመስገን ተስፋዬ፣ ብሩክ ኤርሚያስ፣ ኢዮብ ጌታቸው፣ ላምሮት አረጋኸኝ፣ ኤልሻዳይ ዳዊት እና ኤዶሚያስ ወንድወሰን የተባሉ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።
ፖሊስ በተያዙት ተጠርጣሪዎች ላይ ባደረገው ምርመራ ሟች ዘይኑ ፈድሉ በመንገድ እየተጓዘ ባለበት ወቅት አንገቱን በመያዝና ደረቱን በጩቤ በመውጋት ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረግ ይዞት የነበረውን ሳምሰንግ ስልክ ወስደዋል።
የሟችን አስክሬን ኤርሚያስ አሠፋ በተባለው ግለሠብ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-B 83677 አ/አ ቪትስ ኮምፓክት ተሽከርካሪ ኮፈን ውስጥ በመክተት ሌሎቹ ተጠርጣሪዎች ደግሞ ኮድ 3-71724 አ/አ በሆነ ቪትስ ተሽከርካሪ በመሆን ተከታትለው በመሄድ የሟችን አስክሬን ድልድይ ስር ጥለውት መሄዳቸውን በምርመራ ወቅት ገልጸዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ወንጀሉን በፈጸሙ 48 ሠዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በፖሊስ እንደተያዙ እና በራሳቸው ፍላጎት ወንጀሉን እንዴት እንደፈፀሙ መርተው ማሳየታቸውን ከምርመራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ፖሊስ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ባደረገው ምርመራ የማስፋት ስራ ለወንጀሉ መፈፀሚያ የሚጠቀሙበት 2 ጩቤ፣ 3 ሽጉጥ መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ገልፆ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራው እንደቀጠለ ገልጿል።
የሟች ዘይኑ ፈድሉ ቤተሰቦች በበኩላቸው በወንድማቸው ህልፈት እጅጉን ማዘናቸውን ገልጸው ፖሊስ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወንጀል ፈፃሚዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
አዲስ ፖሊስ

23 days ago