Logo
SeledaPost
ዶናልድ ትራምፕን የምትመስለው ስፔናዊቷ ገበሬ የመገናኛ ብዙኃን መነጋገሪያ ሆናለች!

በሰሜን ምዕራብ ስፔን ገጠራማ ስፍራ (ጋሊሲያ) የምትኖረው ዶሎሬስ ሌይስ አንቴሎ የተባለችው አዛውንት፣ ከአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ባላት አስገራሚ መመሳሰል የተነሳ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በድጋሚ ከፍተኛ ትኩረት እየሳበች ትገኛለች።

እ.ኤ.አ. በ2018 ስለ ገጠር ህይወት የሚዘግብ አንድ ጋዜጠኛ የዕድሜ ባለጸጋዋን ዶሎሬስን በፈረንቃ (አካፋ) ተደግፋ በፎቶ ካሜራው አስቀርቷት ነበር። በፎቶው ላይ ያላት የፀጉር ቀለም፣ የፊት አወቃቀር እና አስተያየት ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ፍጹም አንድ አይነት በመሆኑ በወቅቱ ዓለምን አስገርሞ የነበረ ሲሆን፣ ይህ ምስል አሁን በ2026 በድጋሚ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ በስፋት እየተጋራ ይገኛል።

የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች የሁለቱን ምስሎች ጎን ለጎን በማነፃፀር "መንትዮች ናቸው" እስከማለት ደርሰዋል።

ዶሎሬስ ይህንን አጋጣሚ በጣም በሚያስቅ ሁኔታ የተቀበለችው ሲሆን፣ በወቅቱ ለሀገር ውስጥ ጋዜጣ በሰጠችው አስተያየት፦ "ምስሌ በጣም ሩቅ ቦታ የተጓዘ ይመስላል፤ እኔ እንደማስበው ግን ይህ የሆነው በፀጉሬ ቀለም ምክንያት ነው" ስትል በፈገግታ ተናግራለች።

ይህ ድንገተኛ ዝና በገጠሯ ስፔን የምትመራውን ቀለል ያለ የግብርና ህይወት አላስተጓጎላትም፤ ይልቁንም አሁንም ድረስ በደስታ ስራዋን እየቀጠለች ትገኛለች ነው የተባለው።

Seledadotio
Seledadotio
25 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.