Logo
SeledaPost
በሳውዲ እስር ላይ ለነበሩ 1,971 ኢትዮጵያውያን ምሕረት ተደረገላቸው‼

​ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ፣ በሳዑዲ አረቢያ በሕግ ሂደትና አስገዳጅ እርምጃዎች ውስጥ የነበሩ 1,971 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ባለሥልጣናት የንጉሣዊ ምሕረት አዋጅ (Royal Amnesties) ተጠቃሚ መሆናቸውን አስታወቀ።

​በሪያድ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲና በጅዳ ከሚገኘው ቆንስላ ጄኔራል ጋር በመተባበር የተደረጉት ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች አዎንታዊ ውጤት ማምጣታቸውን የገለጸው ሚኒስቴሩ፣ በምሕረቱ የተካተቱ ዜጎችን ወደ ሀገር ለመመለስ የሚያስችሉ ሥራዎች መጀመራቸውን ጠቁሟል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በውጭ ሀገራት የሚገኙ ዜጎቹን ደኅንነትና መብት ለማስጠበቅ ከሳዑዲ ባለሥልጣናት ጋር የሚያደርገውን ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ንግግር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጧል።

Seledadotio
Seledadotio
25 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.