Logo
YenetaTube
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሆርሙዝ ላይ ለመወያየት ኦማን ገቡ

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ቅዳሜ ዕለት በኦማን ዋና ከተማ ሙስካት ገብተዋል ሲሉ የኢራን የመንግስት ሚዲያዎች ዘግበዋል።
በየካቲት ወር ዩናይትድ ስቴትስ እና እስራኤል ከኢራን ጋር ጦርነት ከገጠሙ ወዲህ የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ በአብዛኛው ተዘግቶ ቆይቷል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢራን እና በአሜሪካ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ከፈረሰ ወዲህ ጉዳዩ እንደገና የዓለም ትኩረት ማዕከል ሆኗል።ቴህራን ከአሜሪካ ጋር በተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት 'ቃሏን ጠብቃለች' ሲሉ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጸዋል።

ኢራን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በተደረገው የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ የገባችውን ቃል አክብራለች ሲሉ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በ X ገፃቸው ላይ ጽፈዋል።«ኢራን እስካሁን ድረስ ቃሏን ጠብቃለች፣ የስምምነቱን አንቀጽ 9 እየጣሰ ካለው የአሜሪካ የግምጃ ቤት ሚኒስትር በተለየ። ይህ ጥሰት በዩናይትድ ስቴትስ ዘንድ ሌሎች ጥሰቶችን እና የተሳሳቱ እርምጃዎችን ያስከትላል። የእውነታ ማረጋገጫው፡ የጋራ ተገዢነት ብቻ ሊኖር ሲችል ነው» ብለዋል አራግቺ።

አሜሪካ እና ኢራን የተኩስ አቁም ስምምነቱን በመጣስ አንዳቸው በአንዳቸው ላይ ጣት መቀሳሰር ይዘዋል።

DW Amharic

27 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.