(ዘ-ሐበሻ ዜና) የዲሞክራቲክ ፓርቲ የኮንግረስ አባል የሆኑት ጂሚ ፓኔታ፣ አሜሪካ ከኢራን ጋር እያደረገች ያለውን ወታደራዊ ግጭት በተመለከተ ዶናልድ ትራምፕን አጥብቀው ተቹ። አስተዳደሩ እየወሰዳቸው ያሉ እርምጃዎች የዲፕሎማሲ እና የስትራቴጂክ እቅድ ውድቀትን በግልጽ የሚያሳዩ መሆናቸውን አስጠንቅቀዋል።
ኮንግረስማኑ በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ፣ "ምንም እንኳን ፕሬዝዳንቱ ስለ ጉዳዩ የሚናገሩትን ማመን ባንችልም፣ አሜሪካ ዳግም የጀመረችውን ጥቃት እና የኢራንን የድሮን ጥቃቶች በመመልከት ብቻ አሁን ያለው ድርድር እና የተኩስ አቁም ስምምነት ምን ያህል ውጤት አልባ እና ጉድለት ያለበት መሆኑን መረዳት እንችላለን" ብለዋል።
አክለውም አሁን የተፈጠረው ቀውስ፣ "ያለ ግልጽ ስትራቴጂ፣ ያለ ኮንግረሱ ፈቃድ እና ያለ አሜሪካ ህዝብ ስምምነት ወደ ጦርነት የመግባት ቀጣይነት ያለው መዘዝ ነው" ሲሉ ገልጸዋል።
ጂሚ ፓኔታ በንግግራቸው "የኮንግረሱ አፈ-ጉባኤ ቢደግፉንም ባይደግፉንም፣ ኮንግረሱ የኢራንን ጦርነት ለማስቆም፣ የሆርሙዝ ሰርጥን ለማስከፈት እና ለአሜሪካውያን የዕቃ ዋጋን ለመቀነስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠል አለበት" በማለት አሳስበዋል።
የኮንግረስ አባሉ ጂሚ ፓኔታ በኦባማ አስተዳደር ዘመን የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር እና የሲአይኤ ዳይሬክተር ሆነው ባገለገሉት ታዋቂው ፖለቲከኛ ሊዮን ፓኔታ ልጅ መሆናቸው ይታወቃል።

29 days ago