Logo
EBC
ፈረንሳይ ሞሮኮን አሸንፋ ለግማሽ ፍፃሜ አለፈች
*****************

በ23ኛው የዓለም ዋንጫ በፈረንሳይ እና በሞሮኮ መካከል የተደረገው የመጀመሪያው የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ፤ በፈረንሳይ 2 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቅቋል።

የፈረንሳይን የማሸነፊያ ግቦች 60ኛው ደቂቃ ላይ ኪሊያን ምባፔ እንዲሁም 66ኛው ደቂቃ ላይ ኡስማን ዴምቤሌ አስቆጥረዋል።

ኪሊያን ምባፔ በዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ታሪኩ ያስቆጠራቸው ግቦች 20 የደረሱ ሲሆን፤ 29ኛው ደቂቃ ላይ ፈረንሳይ አግኝታው የነበረውን ፍፁም ቅጣት ምት ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

ፈረንሳይ በግማሽ ፍፃሜው ከስፔን እና ቤልጂየም አሸናፊ ጋር ትጫወታለች።
#france #morocco #fifaworldcup2026 #quarterfinal #football #sports #ebc

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.