በሮቤ ከተማ የጤና ባለሙያዉን በደቦ በመደብደብ የአካል ጉዳት ያደረሱ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ
በሮቤ ከተማ አስተዳደር አዶሼ ክፍለ ከተማ ሮቤ የተሽከርካሪ መናሕርያ ውስጥ አንድን የጤና ባለሞያ በደቦ የደበደቡ ወጣቶች በእስራት ተቀጡ። እንደ ሮቤ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምርያ የኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ሐላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ጌታቸው ታምሩ ገለፃ 1ኛ ሱልጣን ሑሴን ፣ 2ኛ ኢብራሔም ሑሴን እና 3ኛ ቦንሣ አወሉ የተባሉ ተከሳሾች የአንደኛ ተከሣሽ የእጅ ስልክ ጠፋ በሚል ሠበብ በአንድ የጤና ባለሞያ ላይ በደቦ ከፍተኛ ድብደባ በማድረስ የአካል ጉዳት አድርሰዋል።
ሚያዝያ 8 ቀን 2018 ዓም ከጥዋቱ አንድ ሠዓት ተኩል ላይ አሮጌው መናሕርያ ውስጥ የጊኒር ከተማ ጤና ፅህፈት ቤት የጤና ባለሞያ የሆኑትን ዋቆ ከድር የተባሉትን የአንደኛ ተከሣሽ ሞባይል በመጥፋቱ ወስደኃል በሚል ያልተረጋገጠ ማስረጃ በቡድን ተደራጅተው የድብደባ ወንጀል ፈፅመውባቸዋል።ባልተጣራና ባልተረጋገጠ ጉዳይ በመቀናጀት የፈፀሙት የድብደባ ወንጀል በማሕበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ቁጣ ማስከተሉ ይታወሳል፡፡
ፖሊስም በወቅቱ ሁኔታውን ተከታትሎ የድርጊቱ ፈፃሚ ወጣቶችን በቁጥጥር ስር በማዋል የምርመራ መዝገቡን በተለያዩ ማስረጃዎች በማጣራት መዝገቡን ለአቃቢ ሕግ ልኳል፡፡ አቃቢ ሕግም ከፖሊስ የቀረበውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በውንብድና ወንጀል ክስ መስርቷል፡፡ ክሱን የተመለከተው የሮቤ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓም በዋለው ችሎት እያንዳንዳቸዉን በሁለት ዓመት ከሶስት ወራት እስራት እንዲቀጡ የወሠነባቸው መሆኑ ምክትል ኢንስፔክተር ታምሩ ጌታቸው ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

29 days ago