Logo
Getu Temesgen
ፕሬዚዳንት ትራምፕ የስፔን መንግስት "አስከፊ አጋር" እና "ተስፋ የቆረጡ መሪዎች" በማለት ወረፉ
#ethiopia | በአንካራ እየተካሄደ በሚገኘው የኔቶ ጉባኤ ላይ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስፔን በኔቶ ህብረት ውስጥ ያላትን አቋም እና ለወታደራዊ ወጪዎች ያላትን ዝቅተኛ አስተዋጽኦ ተችተዋል።

ፕሬዝዳንቱ ከስፔን ጋር የነበራቸውን የንግድ ግንኙነት ሙሉ በሙሉ ማቆማቸውን አስታውቀዋል።

የኔቶ አባል ሀገራትም ከስፔን ጋር ማንኛውንም አይነት የንግድ እንቅስቃሴ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

ስፔን በአሜሪካ እና በኢራን መካከል በነበረው ግጭት ወቅት አሜሪካ በስፔን የሚገኙ ወታደራዊ መሰረተ ልማቶች እና የአየር ክልሏን ለወታደራዊ ጥቃት እንዳትጠቀም መከልከሏ ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነቀረውን ግንኙነት አሻክሮት ይገኛል።

የፕሬዝዳንት ትራምፕ ትችት ተከትሎ የስፔን መንግስት የንግድ ፖሊሲዎች የሚወሰኑት በአውሮፓ ህብረት ደረጃ እንጂ በአንድ ሀገር ብቻ እንደማይሆን አስታውቋል።

አሁን እየተካሄደ ባለው የኔቶ ጉባኤ ላይ ይህ መግለጫ በአሜሪካ እና በስፔን እንዲሁም በኔቶ አባላት መካከል ያለውን ውጥረት አባብሶታል ሲል አናዱሉ ዘግቧል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #natoankarasummite #usaspaindisagreement

29 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.