(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሩሲያ በዩክሬይን ዋና ከተማ ላይ ለ2ተኛ ቀን ድብደባ ፈፀመች፡፡ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ባወጣው መግለጫ ዩክሬይን በሰላማዊ መሰረተ ልማቶች ላይ ለፈፀመችው ጥቃት የአፀፋ መልስ መስጠቱን አስታወቀ፡፡ ሚኒስትሩ በዚህ መግለጫው በአፀፋ መልሱ በዋና ከተማዋ ኬይቭ በሚገኙ ወታደራዊ የኢንዱስትሪ ተቋማት ላይ አግባብ ባላቸው መሳሪያዎች ጥቃት ማድረሱን ገልጿል፡፡
በዛሬው ጥቃት ከተመቱት ውስጥ ፍላሚንጎ የተሰኘውን ረጅም ርቀት ሚሳኤል የሚያመርተው ፋብሪካ እንደሚገኝበትም አስረድቷል፡፡ እንዲሁም የድሮን መገጣጠሚያዎች፣ የጦር መሳሪያ መጋዘኖችና ሌሎችም ወታደራዊ ኢንዱስትሪዎችን ኢላማ ማድረጉን አስታውቋል፡፡ ሩሲያ በዋና ከተማዋ ኬይቭ ላይ ዛሬ ይህንን ድብደባ የፈፀመችው ለ2ተኛ ነው፡፡ በትላንትናው እለትም በተመሳሳይ በኬይቭ ላይ ከባድ ድብደባ መፈፀሟ ይታወሳል፡፡
የዛሬውን ጥቃት ለየት የሚያደርገው ፕሬዝደንት ዘለንስኪ በኔቶ ስብሰባ ላይ ተገኝተው ከአሜሪካው አቻቸው ጋር ከመገናኘታቸው ከሰአታት በፊት የተፈፀመ መሆኑ ነው፡፡ ይህንን ጥቃት በተመለከተ የዩክሬይን ባለስልጣናት ባወጡት መግለጫ ድብደባው የተፈፀመው በኬይቭ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ከተሞችም መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በእነዚህም ቢያንስ 3 ሰዎች መገደላቸውንና ከ20 በላይ መቁሰላቸውን አስረድተዋል፡፡ በዛሬው ጥቃት ሩሲያ 169 ድሮኖችንና 7 ሚሳኤሎችን መጠቀሟንም ይፋ አድርገዋል፡፡ በሌላ በኩል የሩሲያ አየር ሀይል በዛሬው እለት 415 የዩክሬይን ድሮኖችን መቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡

1 month ago