የኤርትራ መንግስት ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ዛሬ በፓርላማ ቀርበው ለሰጡት ማብራሪያ እና በተለይ ከኤርትራ (ሻዕቢያ)፣ ከሕወሓት እና ከሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ላነሷቸው ነጥቦች በማስታወቂያ ሚኒስቴሩ በኩል ፈጣንና ጠንከር ያለ ምላሽ ሰጥቷል።
ሁለቱ ወገኖች በቀጠናው ሰላምና በጎረቤት ሀገራት ጣልቃ ገብነት ዙሪያ እርስ በርሳቸው ተቃራኒ የሆኑ ክሶችን ሰንዝረዋል።
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በፓርላማ ንግግራቸው በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ወጣቶችን በጉልበት እያፈሱ ለሱዳን ጦርነት "እየሸጡ" መሆኑን ገልጸዋል።
"የትግራይ ወጣቶች በማያውቁት ጉዳይ በሱዳን ጦርነት ውስጥ ህይወታቸውን እያጡ ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህ ድርጊት የህዝቡን መከራ የሚያባብስ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።
በተቃራኒው የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ ለሱዳን ግጭት መባባስ ተጠያቂው የኢትዮጵያ መንግስት ራሱ ነው ሲል ገልጿል።
ኢትዮጵያ ለሱዳኑ ፈጣን ደጋፊ ኃይሎች (RSF) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ሚስጥራዊ የጦር ሰፈርና ማሰልጠኛ በመስጠት በቀጥታ በጦርነቱ ውስጥ ተሳትፎ እያደረገች መሆኑንና ለዚህም "ግልጽ ማስረጃዎች አሉ" ሲል አጸፋዊ ክስ ሰንዝሯል።
ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ በንግግራቸው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውንም አይነት "ትንኮሳ" ለመመከት መንግስታቸው ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል። የኤርትራ መንግስት በበኩሉ፣ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ህግጋትንና የቀጠናውን ሀገራት ሉዓላዊነት እየጣሰች ያለችው "የባህር በር ባለቤትነት" በሚል በምታሳየው የግዛት ማስፋፋት ፍላጎት ነው ብሏል።
የኢትዮጵያ መንግስት በአንድ በኩል "ጥቃት አድራሽ" በሌላ በኩል ደግሞ "ተጠቂ" ሆኖ የመቅረብ ድራማ እየሰራ ነው ስትልም ወርፋለች።
Seledadotio

1 month ago