ሰላም፤ እንደምን አደራችሁ?
የመደመር መንግሥት በአምስቱ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች ሲመዘን
የመደመር መንግሥት ወደ ሥልጣን ሲመጣ የኢትዮጵያን የምጣኔ ሀብት መዋቅር ካረጀውና በአንድ ዘርፍ ላይ ብቻ ከተደገፈው የግብርና ምህዳር በማውጣት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስትራቴጂን ቀረጸ።
በዚህ ስትራቴጂ ውስጥ አምስት ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች፡ ግብርና፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን፣ አይሲቲ እና አምራች ኢንዱስትሪ ተለይተው ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል።
መንግሥት በነዚህ ዘርፎች የገባውን ቃል እና ባለፉት አምስት ዓመታት የታየውን አፈጻጸም በአጭር በአጭሩ ለማየት እንሞክር፡፡
1. ግብርና፡-
ቃል የተገባው፡ የግብርናውን ዘርፍ ማዘመን፣ የምግብ ዋስትናን (ራስን መቻል) ማረጋገጥ እና ኢትዮጵያን ከእህል አስመጪነት ወደ ላኪነት ማሸጋገር።
አፈጻጸም ፦ ግብርናው በመደመር መንግሥት ስር ትልቅ የመዋቅር ለውጥ ያሳየበት ዘርፍ ነው። በተለይም በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተመዘገበው ውጤት ሀገሪቱን ወደ ስንዴ ላኪነት ያሸጋገረ ታሪካዊ ምዕራፍ ሆኗል።
2. ቱሪዝም ፡-
ቃል የተገባው፦ የቱሪስት መስህቦቻችንን አቧራ አራግፈን አሻራ እናኖራለን በሚል መርህ፣ ዘርፉን የሀገር ገጽታ መገንቢያና የውጭ ምንዛሬ ማግኛ ምሰሶ ማድረግ።
አፈጻጸም ፦ ዘርፉ ከፍተኛ መነቃቃት የታየበት ነው። በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች አማካኝነት እንደ እንጦጦ፣ አንድነት ፓርክ፣ ጎርጎራ፣ ወንጪ እና በቅርቡ የተመረቀው የአርባምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት ያሉን ጨምሮ አዳዲስና ዘመናዊ መዳረሻዎች ተገንብተዋል።
3. ማዕድን ፡-
ቃል የተገባው፦ የሀገሪቱን የማዕድን ሀብት በአግባቡ ማልማት፣ ህገ-ወጥ የማዕድን ዝውውርን መቆጣጠር እና ዘርፉን የብሔራዊ ኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ምሰሶ ማድረግ።
አፈጻጸም ፦ መንግሥት የድንጋይ ከሰል ምርትን በማሳደግ የውጭ ምንዛሪን ለማዳን የጀመረው ስራ እና የወርቅ ግዢ አሰራርን በማዘመን የሀገር ውስጥ ገበያ ድርሻን ከፍ ለማድረግ ያደረገው ጥረት የሚጠቀስ ነው።
4. አይሲቲ እና ዲጂታል ኢኮኖሚ:-
ቃል የተገባው፦ የቴሌኮም ገበያውን ለግሉ ዘርፍ ክፍት ማድረግ፣ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን መተግበር እና የቢሮክራሲ አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ማድረግ።
አፈጻጸም ፦ የመደመር መንግሥት በትልቅ ቁርጠኝነት ካሳካቸው ጉዳዮች አንዱ የኢትዮ ቴሌኮም ሞኖፖሊን ሰብሮ ሳፋሪኮምን ወደ ገበያ ማስገባት እና የዲጂታል ክፍያ ስርዓትን ማስፋፋት ነው። የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ እና የቴሌብር/ባንኪንግ መተግበሪያዎች የዜጎችን የዕለት ተዕለት ሕይወትና የንግድ እንቅስቃሴ አቅልለዋል።
5. አምራች ኢንዱስትሪ:-
ቃል የተገባው፦ የሀገር ውስጥ አምራችነትን ማሳደግ፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካት እና ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠር።
አፈጻጸም ፦ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተከፈተው ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አማካኝነት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት አቅም 58 በመቶ ደርሷል።
በአጠቃላይ ባለፉት አምስት ዓመታት
በአምስቱ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች በመደመር መንግሥት መሪነት የተመዘገቡት ስኬቶች መንግሥት ገቢር-ነበብ እና ተግባር ተኮር መሆኑን ያሳዩ ናቸው።

1 month ago