ሀያላኖቹ ሊመክሩ ነው
#ethiopia | የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርቡ ለመነጋገር መስማማታቸውን ክሬምሊን አስታውቃለች።
የሁለቱ መሪዎች ውይይት የሚደረገው መች እንደሆነ ክሪምሊን አልገለፀም።
ሆኖም በአንካራ ከሚካሄደው የኔቶ የመሪዎች ጉባኤ መጠናቀቅ በኋላ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።
ስማቸው ያልተገለፀ አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን እንደገለጹት ፕሬዚዳንት ትራምፕ በዚሁ ከኔቶ ጉባኤ ጎን ለጎን ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ ጋር ይወያያሉ ብለዋል።
የዚህ ውይይታቸውን ዋና ዓላማም በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል እየተካሄደ ያለውን ጦርነት ለማቆም የሚያስችል ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንደገና ለመጀመር ያለመ ነው ብለዋል።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭም መሪዎቹ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለመቀጠል መስማማታቸውን አረጋግጠዋል።
ትራምፕ ከዘሌንስኪ ጋር ከተወያዩ በኋላ ከፑቲን ጋር በስልክ እንደሚወያዩ የክሬምሊን ቃል አቀባይ አረጋግጠዋል ሲል የፃፈው አርቲ ኒውስ ነው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #kremlinspokesperson #peskove #putintrump #rtnews

1 month ago