Logo
FastMereja
“እናት ፈር ቀዳጅና ለሌሎችም ተሞክሮ የሚሆን ብቸኛው የቀጠናው ሞዴል አካዳሚ ነው” ስንትአየሁ ንብረት

በእንጅባራ ከተማ የሚገኘው አንጋፋው "እናት አካዳሚ" ኬጂ (KG) እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ2018 ዓ.ም ተማሪዎቹን በደመቀ ሁኔታ አስመረቀ።

" እናት አካዳሚ" (KG) እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018 የትምህርት ዘመን ሲያስተምራቸው የቆዩትን ተማሪዎቹን፣ የተማሪ ወላጆች፣ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶችና የአካባቢው ማህበረሰብ በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አስመርቋል።

‎​በምረቃ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የእንጅባራ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ ስንታየሁ ንብረት ፥በእንጅባራ ከተማ ከሚገኙት 12 አካዳሚዎች መካከል "እናት " የነገ አገር ተረካቢ ህፃናትን በትክክለኛው የዕውቀትና የሥነ-ምግባር ማዕቀፍ በመቅረጽ ረገድ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ነው።

‎​እናት ኬጂ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጥራት ባለው ትምህርት ላይ በመረባረብ በተለይም በትውልድ ግንባታ ሂደት ውስጥ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛና ለሌሎችም አርአያ የሚሆን መሆኑን ተናግረዋል።

‎ትምህርት ቤቱ ህጻናትን ከመንከባከብ ባለፈ ለአገር የሚጠቅም ስነ-ምግባር ያለው ትውልድ ለማፍራት የሚያደርገውን ጥረት አጋዥ አካላት ሁሉ ሊደግፉት እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የእናት አካዳሚ መስራችና ባለቤት ጥሩወርቅ ደባሱ፥በዛሬው ዕለት በ3ቱም የአካዳሚው ት/ቤቶች ኬጅ(ቅድመ መደበኛ) ያጠናቀቁ 240 ተማሪዎች ተመርቀዋል።

ትምህርት ቤቱ መደበኛውን የማስተማር ሂደት ብቻ ሳይሆን የተማሪዎችን ስብዕና፣ የቋንቋ ክህሎትና የባህል እሴት ማሳደግ ላይ መስራቱ የነገ አገር ተረካቢ እያፈራ መሆኑ ተናግረዋል ።

አካዳሚው በ2000 ዓ. ም መማር ማስተማር የጀመረ መሆኑን ያስታወሱት ወ/ሮ ጥሩወርቅ በዚህ አመት ለመጀመሪያ ጊዜ 6ኛ ክፍል ተማሪዎችን ክልላዊ ፈተና ማስፈተኑ የዘንድሮን ምረቃት የተለየ ያደርገዋል ብለዋል።

በ2018 ዓ.ም ከ1ሽ 600 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማሩንም ተናግረዋል።

በቀጣዩ የትምህርት ዘመንም የተሻሻሉ አሰራሮችንና ግብዓቶችን በማሟላት በርካታ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስ
ተማርና ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቀዋል።

የተማሪ ወላጆች በሰጡት አስተያየት ‎​እናት ኬጂ (KG) እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት በተማሪዎች ላይ የሚያደርገው ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ አበረታች መሆኑን ገልጸዋል ።

ተቋም በተጠናከረ መልኩ እያሳየ ያለው ጥንካሬና ለትምህርት ጥራት የሚሰጠው ትኩረት ይበልጥ ሊጎላና ሊደገፍ እንደሚገባም ተናግረዋል ።

የዛሬ ህፃናት የነገ ሀገር ተረካቢዎች አለም ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል ከዚህ በላይ ቅደመ መደበኛ ላይ መሰራት እንደሚገባም ጠቁመዋል።

በተማሪዎች የቀረቡ ልዩ ልዩ ዝግጅቶች የምረቃ ስነስርዓቱን አድምቀውታል።
‎​



1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.