Logo
Getu Temesgen
ቴክኖ ኢትዮጵያ የ10 ቀናት የፎቶ ኤግዚቢሽን ሊያዘጋጅ ነው
#ethiopia | ቴክኖ ኢትዮጵያ አዲሱን Camon 50 Pro ስማርት ስልክ በመጠቀም በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተነሱ ፎቶዎችንና ታሪኮችን የሚያቀርብ የ10 ቀናት የፎቶ ኤግዚቢሽን እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

ኤግዚቢሽኑ ከሰኔ 27 እስከ ሐምሌ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ በአዲስ አበባ የህፃናትና ወጣቶች ትያትር ኮምፕሌክስ የሚካሄድ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ጋር በትብብር መዘጋጀቱ ተገልጿል።

የመክፈቻ ፕሮግራሙ ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ በድምቀት እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን፣ ተሳታፊዎች ፎቶዎችንና ታሪኮችን ከመመልከት ባሻገር በዕጣ የCamon 50 Pro ስልክ ተሸላሚ የመሆን እድል እንደሚያገኙም ቴክኖ ኢትዮጵያ አስታውቋል።

ድርጅቱ ዜጎች ከቤተሰብና ከወዳጆቻቸው ጋር በመሆን በፕሮግራሙ እንዲሳተፉ፣ ሀገራቸውን በፎቶ እና በታሪክ እንዲያውቁ፣ እንዲዝናኑ እና የሽልማት እድል እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርቧል።

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.