Logo
EBC
ሀገራዊ ምክክሩ የሀሳብ ብዝኃነትን ለማስተናገድ የፈጠረው ምቹ ሁኔታ የሚደነቅ ነው፦ ምሁራን
****************

ኢትዮጵያውያን በጋራ መምከራቸው የሀሳብ ብዝኃነትን ለማስተናገድ ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ ሀገራዊ ምክክር እስከአሁን የደረሰበት ደረጃ የሚደነቅ ነው ሲሉ ምሁራን ተናገሩ።

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ አበሻ ሽርኮ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነው ሀገራዊ ምክክር የተለያዩ ምዕራፎችን አልፎ ፍሬ ለማፍራት ተቃርቧል።

ሂደቱ የመንግሥት፣ የሃይማኖት፣ የልሂቃን፣ የብሔር ብሔረሰቦች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሌሎች ማህበራዊ መሠረቶችን ጣልቃ ገብነት የማይፈቅድ በመሆኑ በመሆኑ ተቀባይነቱ የላቀ ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል።

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የግብርና ኮሌጅ መምህርና ምክትል ዲን አልማዝ ባልጣ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ምክክሩ የተገለሉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን ጨምሮ ሁሉንም ማህበራዊ መሠረቶች በማሳተፍ እዚህ መድረሱ የሚደነቅ ነው ብለዋል።

ሀገራዊ ምክክሩ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ካለው ቁልፍ ፋይዳ ባሻገር መተሳሰብ እና አንድነትን ለማጎልበትም ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ምሁራኑ ገልጸዋል።

በተመስገን ተስፋዬ
#ethiopia #nationaldialogue #nationalconsensus #peace #unity #ebc

3 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.