Logo
EBC
ኢነርጂ ለሁሉም፦ የኢትዮጵያና የብሪክስ የጋራ ራዕይ
******************

ኢትዮጵያ በህንድ በተካሄደው 11ኛው የብሪክስ የኢነርጂ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ በታዳሽ ኃይል ዘርፍ እያስመዘገበችው ያለውን ተስፋ ሰጪ ዕድገት እና የወደፊት ራዕይዋን በስፋት አስተዋውቃለች።

ሀገራችን እ.አ.አ በ2030 መላው ዜጋ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆን ያስቀመጠችውን ብሔራዊ ግብ ለማሳካት ያላትን ጽኑ ቁርጠኝነት በዚሁ ዓለም አቀፍ መድረክ ላይ በድጋሚ አረጋግጣለች።

በዚሁ መድረክ ላይ ኢትዮጵያ በዘመናዊ የኃይል መረብ ግንባታ፣ በኃይል ማከማቻ ቴክኖሎጂዎች፣ በማስተላለፊያ መሠረተ ልማት እና ከብሔራዊ ግሪድ ውጪ ባሉ የኃይል አማራጮች ላይ በከፍትኛ ደረጃ ኢንቨስት እያደረገች መሆኑን አብራርታለች።

በተጨማሪም የኑክሌር ኃይልን ለሰላማዊ ዓላማ ለማልማት እንዲሁም አረንጓዴ ሃይድሮጅንን ለማዳበሪያ ምርት፣ ለኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እና ለኤክስፖርት ለመጠቀም ሰፊ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑ ተገልጿል።

በሌላ በኩል ህንድ በብሪክስ ማዕቀፍ ስር የዲጂታል ስማርት ግሪድ እና የኃይል ማከማቻ የልህቀት ማዕከል እንዲቋቋም ሃሳብ ያቀረበች ሲሆን፣ በዚህም ማዕከሉ በአባል ሀገራቱ መካከል የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር ለማድረግ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ገልጻለች።

የግል ባለሀብቶችን በስፋት በመሳብ እና ቀጣናዊ የኃይል ትስስርን ይበልጥ በማጠናከር የብሪክስን “ኢነርጂ ለሁሉም” ራዕይ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደምትሠራም አስታውቃለች።

በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #ebc #brics2026 #renewableenergy #greenenergy #smartgrid #sustainability #energyforall

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.