ሰላም፤ እንደምን አደራችሁ?
ብሔራዊ ጥቅሞቻችን.....
በየትኛውም ሀገር ብሔራዊ ጥቅም ለድርድር የማይቀርብ ቀይ መስመር ነው፡፡ አንዲት ሀገር እንደ ሀገር ለመቀጠል፣ ደህንነቷን ለማስጠበቅና የሕዝቧን ሰላም ለማረጋገጥ በፍጹም ለድርድር የማታቀርባቸው እና ለማንኛውም ኃይል በማንኛውም ሁኔታ አሳልፋ የማትሰጣቸው ወሳኝ ጉዳዮች አሉ።
እነዚህ ጉዳዮች በዋናነት ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት፣ የህዝብ ደህንነትና ህልውና፣ ስልታዊ እና የተፈጥሮ ሀብቶች፣ ብሔራዊ ክብርና ታሪክ ዋና ዋናዎቹ ተብለው ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት የሀገርን የመሬት፣ የባህር እና የአየር ክልል ወሰን ሳይደፈር ማስከበር፤ ሀገር እንዳትከፋፈል እና አንድነቷ እንዳይናጋ ማድረግ፤ የውጭ ኃይሎች በሀገር የውስጥ ፖለቲካ እና ውሳኔ ላይ ጣልቃ እንዳይገቡ መከላከልን ያካትታል፡፡
ደህንነት እና ህልውና ሕዝብን ከማንኛውም የውጭ ወረራ፣ ሽብርተኝነት እና የደህንነት ስጋት መጠበቅ፤ የሕዝብን መሰረታዊ የህልውና ፍላጎቶች (ምግብ፣ ውሃ፣ መድሃኒት) የማግኘት መብት ማረጋገጥ እና ሌሎች ጉዳዮችም ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
ስልታዊ እና የተፈጥሮ ሀብቶች ማለት ደግሞ ለሀገር ህልውና ወሳኝ የሆኑ እንደ ወንዞች፣ ማዕድናት እና ስልታዊ መሬቶች ላይ ሙሉ ቁጥጥር እና የባለቤትነት መብትን ማረጋገጥ፣ በራስ ሀብት ላይ የማዘዝ እና ሀገራዊ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎችን ያለ ውጭ ጫና የመቅረጽ መብቶች ናቸው፡፡
የሕዝብ ማንነት እና ባህል የሚንጸባረቅባቸው ብሔራዊ ክብር እና ታሪክ ለብሔራዊ ጥቅም መጠበቅ ወሳኝ ናቸው፡፡ የሀገርን ታሪክ፣ ቅርሶች፣ እሴቶች እና ብሔራዊ ክብር አሳልፎ ካለመስጠት ጋር ስለሚተሳሰሩ፡፡ ሀገራዊ መዳረሻን እና የወደፊት እጣ ፈንታን በራስ ሉዓላዊ ውሳኔ ብቻ የማጽናት ስራ ደግሞ ዋነኛው የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት ነው፡፡
በዚሁ ቅኝት ሀገራት እንደየፍላጎታቸው ለድርድር የማያቀርቧቸው ብሔራዊ ጥቅሞች አሉ፡፡ የአንድ ሀገር ህልውና፣ ደህንነት እና ሉዓላዊነት ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተፅዕኖ የሚያሳርፉ ወሳኝ ጉዳዮች ስለሆኑ።
የግዛት አንድነት እና ሉዓላዊነትን በተመለከተ ቻይናን እንደ ምሳሌ እናንሳ፡፡ ቻይና ታይዋንን እና የደቡብ ቻይና ባህርን በተመለከተ ያላት አቋም ጽኑ ነው። ቻይና ታይዋንን የራሷ አካል አድርጋ ስለምትቆጥር፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ከማንኛውም ሀይል ጋር ለመደራደር ፈቃደኛ አይደለችም። በማንኛውም ዲፕሎማሲያዊ መድረክ ላይ ታይዋንን ነጻ ሀገር አድርጎ የመቀበል ሃሳብ በፍጹም የላትም፤ በዚህ ጉዳይም አትደራደርም።
በተመሳሳይ ኢትዮጵያ በወሳኝ የተፈጥሮ ሀብቶቿ እና የውኃ ደህንነቷ ላይ ብሔራዊ ጥቅሞቼ ብላ ቀይ መስመር አስምራለች፡፡ እነዚህ ሀብቶች ለሀገር ህልውና እና ኢኮኖሚ መሰረት ናቸው፡፡ ኢትዮጵያ የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመገንባት፣ ውኃ የመሙላት እና የመጠቀም መብቷን እንዲሁም ፍትሃዊ የውሃ አጠቃቀም መርህን ለድርድር የማይቀርቡ ብሔራዊ ቀይ መስመሬ ብላ አስቀምጣለች፡፡
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለመውጣት እና የኢኮኖሚ ደህንነትን ለመጠበቅ ስልታዊ የባህር በሮችን ማግኘት ወሳኝ ነው ብላ ታምናለች። የቀይ ባህር መስመር ለዓለም ንግድ ወሳኝ በመሆኑ፣ አካባቢው ካሉ ሀገራት እና በዓለም አቀፍ ኃይሎች ዘንድ የባህር መስመሩን ደህንነት ማስጠበቅ ለድርድር የማይቀርብ ስልታዊ ጥቅም ነው። ኢትዮጵያም ለዚሁ ብላ ነው የባህር በርን ብሔራዊ አጀንዳዋ እያደረገች ያለችው፡፡
ቀይ ባህርን በተመለከተ ግብፅና ኤርትራ “የቀይ ባህር ደኅንነትና አስተዳደር የሚመለከተው ከባህሩ ጋር የሚዋሰኑ (የባህር ዳርቻ ያላቸውን) ሀገራት ብቻ ነው” የሚል ጽኑ አቋም ማራመድ ጀምረዋል፡፡ ይህ ኢትዮጵያን የማግለል ስትራቴጂ ነው፡፡ ይህ የሁለቱ ሀገራት አቋም የኢትዮጵያን የባህር በር ህጋዊ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ የባለቤትነትና የመጠቀም መብት ለመንፈግ ያለመ ነው፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ኢትዮጵያን ከቀጣናው ለማግለል እና ከበባ ውስጥ ለማቆየት የሚደረግ ጥረት ነው፡፡ ይህንንም አቋም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት ሊያወግዘው እና ለብሔራዊ ጥቅሙ በጋራ መቆም ያለበት ጊዜ ላይ እንገኛለን፡፡
የግብፅ ልሂቃን በብዙ ጉዳዮች ላይ ሞቅ ያለ ክርክር ቢያደርጉም በናይል ጉዳይ የተለየ አቋም የላቸውም፡፡ የህልውና ጉዳይ ሆኖ እንደ አስተሳሰብ ተገንብቷል። የተለየ የሚያስብ እንኳን ቢኖር የተወገዘ፤ የተረገመ፤ እንደ ብሔራዊ ጠላት የሚታይ ይሆናል፡፡ ዓባይ እንደ ተራ የፓርቲ መሳሪያ ሳይሆን እንደ ህልውና ጉዳይ ተደርጎ ይወሰዳል። ይህ ወጥነት የግብፅን ስትራቴጂካዊ አቋም አጠናክሯል፡፡
ህንዳውያን በሉዓላዊነት፣ በግዛት አንድነት፣ የኑክሌር መከላከያ ያለልዩነት ይስማማሉ፡፡ ቀይ መስመራቸውም ነው፡፡
እንደነ ሳዑዲ አረቢያ እና ኳታር ያሉ ሀገራት ደግሞ በነዳጅ ሀብታቸው ላይ ያላቸውን ሙሉ የማዘዝ መብት ለውጭ አካል አሳልፈው አይሰጡም።
አሜሪካ በምርጫ ስርዓቷ እና በዴሞክራሲያዊ ተቋሞቿ ላይ የማንኛውንም የውጭ ሀገር ጣልቃ ገብነትን እንደ ብሔራዊ ደህንነት አደጋ ትቆጥራለች። እነዚህ ጉዳዮች ተዛብተዋል ብላ ካመነች በሌሎች ሀገራት ሥርዓት ውስጥም ጣልቃ ለመግባት እንደ ቅድመ ሁኔታ ታስቀምጣቸዋለች፡፡ ቀይ መስመሮቼ ናቸውም ብላ ታምናለች፡፡
ስልታዊ የባህር በር እና የንግድ መስመሮች ላይ የሩሲያን ደግሞ እንመልከት፡፡ ሀገሪቷ ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለመውጣት እና የኢኮኖሚ ደህንነትን ለመጠበቅ ስልታዊ የባህር በሮችን መቆጣጠር ወይም ማግኘት ወሳኝ ነው ብላ ታምናለች። ለዚህም ነው በጥቁር ባህር እና ወሳኝ የዓለም የባህር የመጓጓዟ መስመሮች ላይ ያላትን ድርሻ ማጣት የማትፈልገው፡፡ ራሺያ ከዩክሬን ጋር ላለችበት ግጭት መነሻም ይኸው ነው፡፡
ሌላኛው የአንድ ሀገር የብሔራዊ ጥቅም ቀይ መስመር ማሳያ የፖለቲካ ስርዓት እና የውስጥ ነጻነት ነው፡፡ ይህም የውጭ ሀይሎች የአንድን ሀገር የውስጥ የፖለቲካ ስርዓት ወይም የአመራር መዋቅር እንዲቀይሩ የሚደረግ ጫናን ሀገራት አይቀበሉም። ለዚህ ሰሜን ኮሪያ ጥሩ ምሳሌ ናት፡፡ የራሷን የፖለቲካ ስርዓት እና የኑክሌር እቅዷን ለማስጠበቅ ያላት ጽናት በመሪዎች መለዋወጥ የማይናወጥ ነው። የአሜሪካ እና የዓለም አቀፍ ማዕቀቦች ቢበረቱባትም፣ የሀገሪቱን የፖለቲካ ህልውና አሳልፋ ላለመስጠት የኑክሌር አቅሟን እንደ ዋና ዋስትና አድርጋ ትጠቀማለች። ይህንን አቋሟንም ህዝቧን ከውጭ ወረራ ወይም የህልውና ስጋት ለመጠበቅ ነው ብላ ታምናለች፡፡
በብሔራዊ ደህንነት እና ራስን ከውጭ ጥቃት መከላከል ላይ የእስራኤል አቋም በግልጽ የሚታወቅ ነው፡፡ እስራኤል ደህንነቷን አደጋ ላይ የሚጥል ማንኛውንም የጎረቤት ሀገራት እንቅስቃሴ ለማስቆም ወታደራዊ እርምጃ ከመውሰድ ወደኋላ አትልም፡፡ ይህ ህዝቧን ከውጭ ወረራ ወይም የደህንነት ስጋት የመጠበቅ መብት ነው ብላ ስለምታምን እንደ የመጨረሻ ቀይ መስመሯ አስቀምጣዋለች፡፡
ሀገራት እና ዜጎቻቸው እንደየአውዱ ከላይ በተጠቀሰው መሠረት ብሔራዊ ጥቅሞቻቸውን ለድርድር አያቀርቡም፡፡ በኢትዮጵያ እንደ ብሔራዊ ጥቅም የሚታዩ ጉዳዮች ላይ የእኛ የዜጎች አቋም እንዴት ነው? በብሔራዊ ጥቅሞቻችን ላይ ምሁራኖቻችን፣ የፖለቲካ ተዋንያን፣ ተቋማት፣ ማህበረሰቡ በአጠቃላይ ያለልዩነት ይህ ቀይ መስመሬ ነው አትንኩብኝ የሚለው ጉዳይ ሊኖረው ይገባል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ከሀገር ፍቅር ስሜት ጋር መታየት አለበት፡፡ በዚሁ መሠረት ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን ቆጥረን ቀይ መስመር ማስመር ይገባናል፡፡

1 month ago