ሰላም፤ እንደምን አደራችሁ?
ባለፉት አመታት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሀገር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታዎችን አስገኝቷል፡፡
በኢትዮጵያ ባለፉት አመታት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተለመደው የዕለት ተለት መረዳዳት ባለፈ ሀገር በቀል አቅምን የሚያንቀሳቅስ ትልቅ ብሔራዊ ንቅናቄ እየሆነ መጥቷል፡፡
በኢትዮጵያ ከሚከናወኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እሴቶች ውስጥ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አንዱ ሲሆን አብሮነትን፣ መተሳሰብ እና መረዳዳትን ከማጎልበቱ ባለፈ የሕሊና እርካታ የሚገኝበት መልካም ተግባር ነው፡፡
ይህ ንቅናቄ የሕዝብ ለሕዝብ መተሳሰብን የሚያጠናክር፣ የሀገር አንድነትን የሚያጸና እና የወጣቱን ቁርጠኝነት በተግባር የሚያሳይ ዋነኛ መድረክ ሲሆን፤ በዚህም በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች ወገናቸውን የሚያገለግሉበት ዕድል መፍጠር ተችሏል።
ዜጎች የአቅመ ደካሞችን ቤት መጠገን እና መገንባት፣ ደም መለገስ፣ በችግኝ ተከላ መሳተፍን ጨምሮ በሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች በመሳተፍ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ባሕል አድርገው እያሳደጉ ይገኛሉ።
እነዚህ ተግባራት በማሕበረሰቡ ውስጥ ያሉትን ክፍተቶች በመሙላት ረገድ የማይተካ ሚና አላቸው፤ ይህ አገልግሎት የመንግሥትን የልማት ሸክም ከመቀነስ ባለፈ ጥልቅ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን የሚያጠናክር ነው።
ወጣቶች ከሚኖሩበት አካባቢ እንዲሁም ከዚያ አልፈው በሌሎች አካባቢ ጭምር የተለያየ ቋንቋ እና ባህል ካላቸው ማሕበረሰቦች ጋር በጋራ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመስጠት በሕብረሰተቡ መካከል ጠንካራ የመተሳሰብ ድልድይ እንዲገነቡ አስችሏቸዋል።
በአስቸጋሪ የክረምት ወራት የአንዱ ችግር የሌላውም ህመም መሆኑን በመረዳት እርስ በርስ መደጋገፍ የዘመናት አብሮነትን በማደስ ኢትዮጵያዊነትን በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆም ተግባር ሲሆን÷ መተሳሰብ፣ ክፉ ቀናትን በጋራ የማለፍ ባህልን በማዳበር የሀገርን ሰላምና አንድነት በላቀ ደረጃ ያጠናክረዋል።
አሁን ላይ ወጣቱ ትውልድ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የሚያሳየው ከፍተኛ ተነሳሽነት፣ ስለ ሀገሩ የሚያስብና ኃላፊነት የሚሰማው ዜጋ እየተፈጠረ መሆኑ ማረጋገጫ ነው።
ወጣቶች ዕውቀታቸውን፣ ጉልበታቸውንና ጊዜያቸውን ያለምንም ክፍያ ለሀገራቸው በመስጠት፣ የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያን በመገንባት ለሀገር ዕድገት ያላቸውን ቀዳሚ ሚና እየተወጡ ይገኛሉ።
ይህ ንቅናቄ ማሕበራዊ ውበት ብቻ ሳይሆን፣ የሀገርን ኢኮኖሚያዊ ጫና በከፍተኛ ደረጃ ማቃለል የቻለ ነው፤ ዜጎች በሚሰጡት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ብቻ ከመንግሥት እና ከሕብረተሰቡ ሊወጣ የነበረን በቢሊየን የሚቆጠር ሀብት እያዳነ ይገኛል።
በኢትዮጵያ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ የሚታየው የዜጎች ከፍተኛ ተነሳሽነት በተለይም ወጣቱ ትውልድ የነገዋን የበለጸገች ኢትዮጵያን በገዛ እጁ የሚቀርጽ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡
በጎ ፈቃድ ብሔራዊ አንድነትን በማጥበቅ እና ሕዝብን ከሕዝብ በማስተሳሰር ረገድ የሚጫወተው ሚና በቀላሉ የሚገመት አይደለም።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ጎሮ ወረዳ የዘንድሮውን የክረምት የበጎ ፈቃድ ዘመቻ ባለፈው ሳምንት በይፋ ሲያስጀምሩ÷ የሚሰራ እጅ፣ የሚናገር አፍ፣ የሚያስብ አእምሮ ሲሰናሰሉ ነው ልማት እና ለውጥ የሚመጣው ብለዋል።
ስለዚህ የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራዎቻችን ከበጀት እና ከልማት በላይ ሆነው፤ በመልካምነት ቁም ነገር ሰርተን እንድናልፍ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅብናል።
ወጣቶች የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራዎችን እንደ ታላቅ የክብር ሥራ ወስደው ሲሰሩ÷ አዛውንቶች ደግሞ በዚያ ውስጥ ባህልንና ቋንቋን ማስተማር አለባቸው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት፥ ከሥራ ውጪ የሚገነባ ሀገር እንደሌለና ተባብሮ መስራት ከተቻለ በታሰበው መንገድ የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

2 months ago