የቀድሞ ህወሓት ቡድን የትግራይ ክልልን ለኢኮኖሚና ለሰላም ቀውስ ዳርጓል - አቶ አታክልቲ ኃ/ሥላሴ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በትግራይ ክልል እየታየ ያለው የሰላም መደፍረስ የሥራ አጥነት ችግር እና የኢኮኖሚ ቀውስ እያስከተለ ነው አሉ በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የመቐለ ከተማ የቀድሞ ከንቲባ አታክልቲ ኃ/ሥላሴ።
አቶ አታክልቲ ከፋና ፖድካስት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ የቀድሞ ጽንፈኛ የህወሐት ቡድን ከውጭ ኃይሎች ጋር በመተባበር የክልሉን ሕዝብ ለከፋ ስደትና ጦርነት እየዳረገ ነው ብለዋል፡፡
የትግራይ ሕዝብ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ሲያስከብርና ሲጠብቅ የቆየ የሀገር ባለውለታ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
አሁን ላይ ቡድኑ በትግራይ ሕዝብ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃትና በደል ሲያደርሱ ከቆዩት የሻዕቢያ ኃይሎች ጋር በማበር ታሪካዊ ክሕደት እየፈጸመ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
በትግራይ ክልል ሕዝብ ስም የሚነግደው የቀድሞ የህውሓት ቡድን፥ የወጣበትን ማሕበረሰብ የማይመስል፤ የማይወክል እና የሕዝብ ጉዳት የማይገደው ጸረ ሕዝብ መሆኑን አስረድተዋል።
ቡድኑ የክልሉን ሰላም በማደፍረስና ሕዝብን በማስጨነቅ ዕድሜውን ለማራዘም ሆን ብሎ እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁመው÷ በዚህም ሳቢያ በርካታ ወጣቶችን በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ ጦርነት እንዲማገዱ እያደረገ ነው ብለዋል፡፡
የቀድሞ የህወሓት ቡድን ከጦርነቱ ያመለጠውን የሕብረተሰብ ክፍል ዳግም በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ሕገ ወጥ ስደት እንዲያመራ፥ በዚህም በክልሉ ጠያቂ ወጣቶችና ምሁራንን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት አቅዶ እየሰራ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡
በበጸሎት መንገሻ
አቶ አታክልቲ ኃ/ሥላሴ ከፋና ፖድካስት ጋር ያደረጉትን ቆይታ ለመከታተል ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ፡-https://youtube.com/watch?...

2 months ago