ሁለገቡ አርቲስት ሰማህኘ በለው ዛሬ
ቅዳሜ በባህር ዳር ከተማ ይታወሳል !
የጎጃም ግሸ አባዩ ፈርጥ : የባህል አምባሳደሩ : የሀገር ባለውለታው ሁለገቡ አርቲስት ሰማህኘ በለው ተወልዶ ባደገባት ገፅታዋንም በጥበብ ስራው ሲገነባት በኖረው ባህር ዳር ከተማ ይዘከራል ::
የአርቲስቱ የልጀነት ጓደኞች : ቤተሰቦች : የጥበብ ቤተሰቦች እና አድናቂዎች በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 13 ቀን 2018 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ የክብር ስንብትና የምስል ሃዘን ዝግጅት ይታወሳል ።
የዝግጅቱ ዋና አስተባባሪ ፕሮሞተር ደመወዝ ገነቱ መርዓ ግብሩ እንደሚከተለው መዘጋጀቱን ገልፆል ።
🔘የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ የሃዘን ስሜቱን በሚገልጽ አለባበስ (ጥቁር በመልበስ) ከጠዋቱ 2:00 ላይ በባህር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት፣ ከአዲስ አበባ የሚመጡትን የሟችን ባለቤት ወይዘሮ ገበያነሽ አባተ እና ልጁ ቢኒያም ሰማኸኝን ጨምሮ የሟች ጓደኞቹን ይቀበላል ።
🔘የከተማዋ ነዋሪ በቀድሞው አፄ ቴዎድሮስ ስታዲየም ወይም በጃካራንዳ ሆቴል ፊት ለፊት ቅዳሜ ጠዋት 2:30 ሰዓት ላይ ይሰበሰባል።
🔘 ነዋሪው የሟች ቤተሰቦችና እንግዶች በማርሽ ባንድ በሃዘን ዝግታዊ ድባብ ታጅበው በከፍተኛ የሃዘን ድባብ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንና ወደ አደባባዩ የሚወስደውን የክብር ጉዞ ያደርጋሉ።
🔘በባህር ዳር ከተማ ህዝብ ጥንታዊና ጥልቅ የልቅሶ ባህል፣ ወግና ስርዓት መሠረት፣ ለታላቁ አርቲስት ሰማኸኝ በለው ልብን የሚነካና የህዝብን ስብራት የሚገልጽ የሙሾና የልቅሶ ስነ-ስርዓት ይከናወናል።
🔘የባህል የኪነ-ጥበብ ሰማይ ኮከብ የነበረው የአርቲስት ሰማኸኝ በለው፣ ለሀገርና ለወገን ያበረከተው ታላቅ አስተዋጽኦ፣ ያሳለፈው ውጣ ውረድና አጠቃላይ የህይወት ታሪኩ ለሃዘንተኛው ይነበባል።
🔘ውድ ህይወቱን ለጥበብ በሰጠው አርቲስት መታሰቢያ ላይ፣ በሀገር ታዋቂ ሰዎች፣ የስራ ባልደረቦቹ፣ ቤተሰቦቹና ጥልቅ ሃዘን በገባቸው አድናቂዎቹ አማካኝነት የክብር የአበባ ጉንጉን ይቀመጣል።
🔘የሟች ነፍስ በሰላም እንድታርፍ፣ በሃይማኖቱ መንፈሳዊ ህግና ስርዓት መሠረት ታላቅ የፍትሃት ጸሎት በሃይማኖት አባቶች ይመራል።
🔘ስለ አርቲስት ሰማኸኝ በለው መልካምነት፣ ሰብዓዊነትና ታላቅነት በህይወት በነበረበት ጊዜ አብረውት የነበሩ የቅርብ ወዳጆቹ፣ የሙያ አጋሮቹ፣ የቤተሰብ አባላትና የልብ ጓደኞቹ ልብ የሚነካ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ።
🔘 እንዲሁም ሌሎች የአዳራሽ ልዪ ልዪ ፕሮግራሞች እንደሚኖሩ ታውቋልደ
🔘መላው የባህር ዳር ከተማ ነዋሪ ለአርቲስቱ
የመጨረሻውን ክብር እንድትሰጡ ኮሚቴው ጥሪውን ያስተላልፋል።
"የጥበብ ሰው አይሞትም፣ በስራዎቹ ሁልጊዜም በልባችን ይኖራል!"
ኮሚቴው...

2 months ago