በጋብቻ ውስጥ በግብይት የተገኙ ንብረቶች የግል ወይንስ የጋራ?
ጠበቃና የህግ አማካሪ ፋንታሁን ደለለው
መግቢያ #ethiopia | በጋብቻ ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ አለመግባባቶችን ቀድሞ ለመከላከል እንዲሁም ንብረቶችን ሰላማዊ በሆነ መንገድ በህግ እውቅና ተሰጥቶት ለማስተዳደር የግልና የጋራ ንብረቶችን በህግ አግባብ በመለየት ማስተዳደሩ ለጤናማ የትዳር ህይወት ቀዳሚ መፍትሄ ነው።
1. በግብይት የተገኙ ንብረቶች ማለት ምን ማለት ነው።
በግብይት የተገኙ ንብረቶች ማለት በፌደራል የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ 58 መሠረት አንድ የትዳር አጋር የግል ንብረቱን በጋብቻ ውስጥ እያለ በመሸጥ ሌላ የሚገዛው ንብረት ነው። የግል ንብረት ሲባልም ህግ የአንዱ ተጋቢ የግሉ ንብረት ስለመሆኑ ህጋ ጥበቃ ያደረገለት ነው። ይህንን ቀጥሎ የምንገልጸው ይሆናል።
2. የአንዱ ተጋቢ የግል ንብረት ማለት ምን ማለት ነው?
የተጋቢ የግል ንብረቶች አስቀድሞ ከመጋባታቸው በፊት በእያንዳንዳቸው ያፈሩት ወይም ያለግብይት የተገኙ ንብረቶች ናቸው። እነዚህን አጠር ባለ መንገድ እናስረዳ።
2.1 ተጋቢዎች አስቀድመው ከጋብቻ በፊት ያፈሩዋቸው ወይም የግላቸው ነው በማለት እንዴት ይገለጻል?
እነዚህ ንብረቶች አስቀድመው በየግላቸው ያፈርዋቸው ንብረቶች ሲሆን በጋብቻ ውላቸው ፈቀደው እና ወደው የጋራቸው እንዲሆን ካልፈቀዱ በቀር የግላቸው ሆኖ የሚቀጥሉ ሲሆኑ በስጦታ ወይም በውርስ ያገኙአቸው ከሆኑም የግል ንብረት ተደርገው ይቆጠራሉ።
ይህም ሲባል የአንዱ ተጋቢ የግል ንብረት ማለት በዚህ በተሻሻለው ህግ አንቀጽ 57 መሠረት ያለግብይት ብሎ የሚያስቀምጣቸው ተጋቢዎች ጋብቻ ሲፈጽሙ አስቀድሞ የነበርዋቸው ንብረቶች፣ በውርስ፣በስጦታ የሚያገኝዋቸው ንብረቶች ያለግብይት የተገኙ የግል ንብረቶች ሲሆኑ የጋራ እንዲሆኑ ካልፈቀዱ በቀር የግላቸው ሆነው ይቀጥላሉ።
3. በጋብቻ ውስጥ በግብይት የተገኙ ንብረቶች
ተጋቢዎች የግል ንብረቶቻቸውን በተለያየ ምክንያት ሸጠው በሌላ ንብረት ለመለወጥ ሀሳብ ሲመጣላቸው ሸጠው ለመቀየር ይፈልጋሉ። በዚህን ጊዜ ማድረግ እንደሚችሉ በቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 58/1/ ላይ ተቀምጧል። ምክንያቱም የራስን ንብረት መሸጥ መለወጥ ህገመንግስታዊ መብት እንደ መሆኑ መጠን
ይህን ማድረግ ይችላሉ።
ይሁን እንጂ ይህን ሲያደርጉ ወይም የግል ንብረታቸውን ሽጠው
ሌላ ንብረት ሲገዙ የተገዛውን ንብረት በግል ለማስቀጠል ህጉ ግዴታ ይጥልባቸዋል። ይህም የተገዛውን ንብረት በፍርድ ቤት የግል ስለመሆኑ ማጸደቅ ይጠበቅባቸዋል። የሚያጸደቁትም በፍርድ ቤት ሊሆን የሚገባ ነው።
እዚህ ላይ እንግዲህ ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት መጥቶ እንዲጸድቅ
አቤቱታ ሲቀርብ አመልካች አንዳቸው በግብይት የቀየሩት ሲሆኑ አንዳቸው ተጠሪ ሌላ የትዳር አጋራቸው መሆናቸው የሚካድ አይደለም። ተጠሪ በአቤቱታው ላይ ባይኖር እንኳን ፍርድ ቤት በዚህ አግባብ መልስ አንዲሰጡበት አድርጎ ማጣራት ይጠበቅበታል። ለዚህም ዋናው ምክንያት ንብረቱ የሌላው መብት ይኖርበታል በሚል ነው።
4. ስለዚህ የግል ንብረቱን ሸጦ አዲስ ንብረት የሚገዛው ተጋቢ ማድረግ ያለበት ምንድ ነው?
ይህ የግል ንብረቱን ሽጦ ለመቀየር ያሰበው ተጋቢ በመጀመሪያ ደረጃ ከመሸጡ በፊት ሁነኛ ማስረጃ በእጁ ሊኖር ይገባል። ለምሳሌ ቤት ከሆነ የራሱ ስለመሆኑ የሚያሳይ የቤቱ ማረጋገጫ ካርታ ፣ ሊዝ ፣ሰነዶች፣ የመሳሰሉት እንዲሁም ቀድሞ ንብረቱ የግሉ የሆነበት አግባብ በስጦተ፣በውርስ፣የሚለውን የሚያሳይ ማስረጃ ሊኖረው ይገባል።
እነዚህን ማስረጃዎች ኮፒ በማድረግ መያዝ የሚጠበቅበት ሲሆን ሲሸጠው እነዚህን ማስረጃዎች በመጥቀስ ህጋዊ ውል ሊያደርግ ይገባል። ይህም ውል ወሳኝ ራሱ ብቻ ራሱ ብቻ ሻጭ መሆኑን የሚያሳይ ነው። ሲቀጥል ከገዢ የተላለበት የሽያጭ ገንዘብ የባንክ መግለጫ/statement/ የሚያስፈልግ ሲሆን ሌሎችም የስም ዝውውር ከማድረግ ጋር ተያይዞ አስፈላጊ ናቸው የሚባሉትን ማስረጃዎች በመያዝ ለፍርድ ቤት ከግል ንብረት የተገኘ ንብረት ስለመሆኑ በማስረዳት ማጸደቅ የሚቻል ነው።
5. የጹህፉ ማጠቃለያ እና የህግ ምክር
ተጋቢዎች የግል ንብረቶቻቸውን ሽጠው ሌላ ከመግዛታቸው
በፊት የህጉን አካሄድ እና ውጤት በሚገባ አውቀው ግብይት ሊፈጽሙ እንደሚገባ እና ለዚህም የህግ ባለሙያ በማማከርም ጭምር ማድረግ ይገባል።
ማጣቀሻ/references/
የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ
https://www.facebook.com/s...
https://t.me/Fantahunlawye...
0929101037,0983337690

2 months ago