የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ከፍታ...
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት እና የዲፕሎማሲ ታሪክ በቅርብ ዓመታት ውስጥ በርካታ አመርቂ ስኬቶችን እያስመዘገበ ይገኛል።
ኢትዮጵያ በተለይም በፈታኝ ቀጣናዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች ውስጥ አልፋ ሚዛናዊ፣ አጋርን ማብዛት ላይ ያተኮረና ሀገራዊ ጥቅምን ያስቀደመ ተራማጅ የውጭ ግንኙነት ፍልስፍና በመከተሏ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ቅቡልነት እና ተደማጭነት ከፍ አድርጋለች።
በዚህም በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተሳትፎ በርካታ ስኬቶች ማስመዝገብ ችላለች።
ከእነዚህም መካከል ኢትዮጵያ የብሪክስ ጥምረትን ሙሉ አባል ሆና መቀላቀሏ በታሪኳ ያገኘችው ታላቅ የዲፕሎማሲ ስኬት እና የታሪክ አሻራ ነው።ይህም በማደግ ላይ ካሉ ሀገራት ጋር ያላትን የኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግሮታል።
እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት (ተመድ) የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት አባል ሆና መመረጧ በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ መስክ ያላትን ሚና ከፍ አድርጎታል።
ኢትዮጵያ ከፈረንጆቹ 2026 ጀምሮ የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤትን በሊቀመንበርነት እንድትመራ መመደቧ በአህጉሪቱ ሰላም ማስከበር ላይ ያላትን ቁልፍ ሚና ያሳየ የዲፕሎማሲ ስኬቷ ነው።
በሁለትዮሽ ግንኙነትና ስትራቴጂካዊ አጋርነት ላይ ኢትዮጵያ ከተለያዩ ሀገራት ጋር ያላትን ትስስር አጠናክራለች።
በዚህም በቅርቡ የኢትዮጵያ እና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባደረጉት ውይይት በኢኮኖሚ፣ በደህንነት እና በቀጣናዊ ሰላም ዙሪያ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል።
ከሕንድ ጋር ያላት ግንኙነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ያደገ ሲሆን÷ ከገልፍ ሀገራት ጋርም በቴክኖሎጂ ሽግግርና በኢንቨስትመንት ዙሪያ ሰፊ ትብብሮችን መፍጠር ችላለች።
በተጨማሪም ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ሁለንተናዊ ትስስር ከማጠናከር ባሻገር፣ የአንካራው ስምምነት አማካኝነት የተመዘገቡት ስኬቶች በቀጣናው መረጋጋትን የፈጠሩና የኢትዮጵያን ጥቅም ያስከበሩ ነበሩ።
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ያስመዘገበቻቸው የልማት ስኬቶች ለውጭ ዲፕሎማሲዋ ጥንካሬ እንደጀርባ አጥንት አገልግለዋል።
ኢትዮጵያ ለስንዴ ምርትና ለምግብ ዋስትና የሰጠችው ትኩረት ዓለም አቀፍ አድናቆትን ከማስገኘት ባሻገር ከጣሊያን መንግሥት ጋር በመተባበር 2ኛውን የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባዔን በአዲስ አበባ እንድታስተናግድ በር ከፍቷል።
ዓለም አቀፍ አጀንዳ መሆን የቻለው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርም ወደ ሀገር ውስጥ የሚመጡ የዓለም መሪዎችና ዲፕሎማቶች በዚህ መርሐ ግብር ላይ እንዲሳተፉ በማድረግ የሀገሪቱን መልካም ገጽታ ለመገንባት በከፍተኛ ሁኔታ ጥቅም ላይ ውሏል።
ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ እና መሰል ታላላቅ መድረኮችን በስኬት ማስተናገድ መቻሏ ኢትዮጵያን ብሎም አዲስ አበባን የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ማዕከልነት ይበልጥ ያጠናከረ ነው።
በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲም ኢትዮጵያ በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገብ ችላለች፤ በዚህም ባለፉት አጭር ጊዜያት ብቻ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ከተለያዩ ሀገራት ወደ ትውልድ ቀያቸው በሰላም መመለስ ተችሏል።
በአጠቃላይ መንግሥት የተከተለው ዘመናዊ የዲፕሎማሲ አካሄድ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን፣ ሉዓላዊነቷንና የግዛት አንድነቷን አስከብራ እንድትቀጥል እና በዓለም አቀፍ መድረክ ያላት ተደማጭነት ይበልጥ እንዲጎለብት አስችሏል።
በሶስና አለማየሁ

15 hours ago