የኢትዮጵያ ጉምሩክ ዲጂታል ሲስተም መስተጓጎል፤ አስመጪዎች ለከፍተኛ ኪሳራ መዳረጋቸውን ገለጹ
#fastmereja | የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን በመጠቀም ላይ ያለው የኤሌክትሮኒክ ሲስተም (Electronic Single Window - ESW) መስተጓጎል፣ ዕቃዎችን ወደ ሀገር ውስጥ የሚያስገቡ አስመጪዎችን ለከፍተኛ የንግድ ኪሳራ እና እንግልት መዳረጋቸውን ገለጹ።
በሲስተሙ ላይ በተፈጠረው የቴክኒክ ችግር ሳቢያ የንግድ እንቅስቃሴው ሙሉ በሙሉ መስተጓጎሉን አስመጪዎች ገልጸዋል። የጉምሩክ ኮሚሽን ለላኪዎች (Exporters) በማንዋል (በእጅ) እንዲስተናገዱ መመሪያ ቢሰጥም፣ አስመጪዎችን ያገለለ አሰራር መዘርጋቱ ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሯል።
አስመጪዎቹ በገጠማቸው ችግር የተነሳ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦ በውድ የውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ዕቃዎች በወቅቱ ባለመውጣታቸው፣ በየወደቡና በማከማቻዎች እየተበላሹና ለጉዳት እየተዳረጉ ነው። ላኪዎች በማንዋል እንዲስተናገዱ ተፈቅዶላቸው፣ አስመጪዎች በተመሳሳይ ዕድል አለመስተናገዳቸው አድልኦ የተሞላበትና የንግድ ሰንሰለቱን የሚያስተጓጉል መሆኑን በመግለጽ ላይ ናቸው።
በጉምሩክ መሥሪያ ቤቶች እና በባንኮች ለረጅም ሰዓታት በመሰለፍ ለከባድ እንግልት ተዳርገዋል።
ጉዳዩን የሚከታተሉ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ የጉምሩክ እና የባንክ አሰራር መጓተት በአስቸኳይ ካልተቀረፈ፣ በሀገሪቱ የገበያ አቅርቦት ላይ እጥረት በመፍጠር በዋጋ ንረት ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጥራል።
አስመጪዎች በበኩላቸው፣ ለላኪዎች የተሰጠው አማራጭ ለራሳቸውም እንዲፈቀድ እና መንግሥት የዜጎችን ንግድ ከኪሳራ የሚታደግ ፈጣን መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። እስካሁን በጉምሩክ ኮሚሽን በኩል ስለ ጉዳዩ የተሰጠ ተጨማሪ ማብራሪያ የለም።

2 months ago