(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በከቀናት በፊት ቅሬታቸውን ሲገልጹባቸው ወደ ነበሩት የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ትኩረታቸውን በማዞር ኔታንያሁ "ጥሩ ሰው" መሆናቸውን ቢገልጹም፣ ነገር ግን "አንዳንዴ ትንሽ ስሜታዊ ይሆናሉ" ሲሉ ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ኔታንያሁ አሁን ከሚከተሉት መንገድ ይልቅ "ትንሽ ለዘብ ያለ አካሄድ" ቢጠቀሙ የተሻለ እንደሚሆን ጠቁመዋል። አክለውም፣ "ከሂዝቦላህ የሆነ ሰው ወደ አንድ ህንፃ በገባ ቁጥር፣ ህንፃውን ሙሉ በሙሉ ማፍረስ አይጠበቅብዎትም" በማለት የእስራኤልን ወታደራዊ እርምጃዎች በተዘዋዋሪ ተችተዋል።
አክለውም ትራምፕ በአሜሪካ እና ኢራን መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት በንግግራቸው የዳሰሱ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2020 የኢራኑ ከፍተኛ ጀነራል ቃሲም ሱሌማኒ የተገደሉበትን ጥቃት አስታውሰዋል።
ፕሬዝዳንቱ የኦባማ አስተዳደር ከኢራን ጋር ተፈራርሞት የነበረውን የኒውክሌር ስምምነትም በጽኑ ተችተዋል። ስምምነቱ ኢራን "ወደ ኒውክሌር ጦር መሳሪያ እንድታመራ መንገድ የሚከፍት ነበር" በማለት የራሳቸውን አስተዳደር የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ትክክለኛነት ሞግተዋል።

2 days ago