የጂ-7 መሪዎች በሊባኖስ “አስቸኳይ የተኩስ አቁም” እንዲደረግ በጋራ መግለጫቸው ጠየቁ
በፈረንሳይ እየተካሄደ በሚገኘው የጂ-7 ጉባኤ ማጠቃለያ ቀን ዛሬ ጠዋት የዓለም መሪዎች ባደረጉት ስብሰባ፣ በሊባኖስ “አስቸኳይ የተኩስ አቁም” እንዲታወጅ በጋራ መግለጫቸው ጥሪ አቅርበዋል።
“በሊባኖስ አስቸኳይና ጠንካራ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እንደግፋለን፤ ይህም የሂዝቦላህን ትጥቅ ለመፍታት፣ የመሣሪያ ይዞታ በሀገሪቱ ህጋዊ መዋቅር ስር ብቻ እንዲሆን ለማድረግ እና ተገቢው ዓለም አቀፍ የደህንነት ዋስትና ተሰጥቶት የሊባኖስ የግዛት አንድነትና ሉዓላዊነት እንዲጠበቅ የሊባኖስ መሪዎች ለሚያደርጉት ጥረት እገዛ ያደርጋል” ብለዋል መሪዎቹ ባወጡት የጋራ መግለጫ ፡፡
የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ፣ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጠላትነት ለማስቆም በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተደረሰውን የመግባቢያ ስምምነት «ሁኔታዎችን ሙሉ በሙሉ የሚቀይር» ሲሉ ገልጸውታል።
በፈረንሳይ በተካሄደው የጂ7 (G7) ጉባኤ ማጠናቀቂያ ቀን ለሲኤንኤን በሰጡት መግለጫ፦ «ይህ ለዚህ ወቅታዊ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን... በስብሰባው ላይም እንደታየው፥ ጥቂት ወደኋላ አፈግፍገን ዩክሬንን በአዲስ መልክ እንድንመለከት ያስችለናል።» ብለዋል።
ማርክ ካርኒ በዋሽንግተን እና በቴህራን መካከል የተደረሰውን ጊዜያዊ ስምምነት ቅጂ ማየታቸውን የተናገሩ ሲሆን፥ ስምምነቱ አሜሪካ በኢራን ወደቦች ላይ የጣለችውን የባህር ላይ እገዳ በአስቸኳይ እንድታነሳ እና የሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ እንደገና እንዲከፈት የሚጠይቅ መሆኑ ዘጋርዲያን አስነብቧል።
«እውነቱን ለመናገር፣ ከጠበቅኩት በላይ ሆኖ አግኝቼዋለሁ» ብለዋል የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ ።
የስምምነቱ ዝርዝር ሁኔታዎች ለሕዝብ ይፋ ያልተደረጉ ሲሆን፥ ካርኒ «የራሳችን ምንጮች አሉን» ከማለት ውጪ የውሉን ቅጂ እንዴት ሊያገኙ እንደቻሉ አልገለጹም።
አክለውም ስምምነቱ «ኢራን የኑክሌር መሣሪያ እንዳይኖራት ለማድረግ መሠረት ይጥላል» ካሉ በኋላ፦ «አሁን ወደኋላ የማይመለስበት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል» ብለዋል።
ሜሮን ገብሬ

2 months ago