ኩባንያችን የቴሌኮም እና ዲጂታል ደኅንነትን ለማረጋገጥ ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ለፍትሕ ተቋማት ሰጠ!
ኩባንያችን ኢትዮ ቴሌኮም የሀገሪቱን የዲጂታል ደኅንነት ለማስጠበቅ እና የቴሌኮም መሠረተ ልማቶችን ከጥቃት ለመከላከል እንዲቻል፣ ከተለያዩ የፍትሕ ተቋማት ለተውጣጡ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሀገር አቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና በተለያዩ ከተሞች ሰጥቷል።
“የኢትዮ ቴሌኮም እና የፍትሕ ተቋማት ጥምረት ለዲጂታል ኢትዮጵያ ደኅንነት” በሚል መሪ-ቃል በድሬደዋ፣ በሐዋሳ እና በአዳማ ከተሞች በተካሄዱት በእነዚህ የሥልጠና መድረኮች ላይ፤ ከፌዴራልና ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ በአጠቃላይ 171 ዳኞች፣ አቃቤያነ ሕግ እና የፖሊስ አባላት ተሳትፈዋል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናው ኩባንያችን የሦስት ዓመት ስትራቴጂውንና የኢትዮጵያን የዲጂታል ሽግግር ለማፋጠን ከሚያደርገው ግዙፍ የ4ጂ እና 5ጂ ኔትወርክ መሠረተ ልማቶች ማስፋፊያ ባሻገር የእነዚህን መሠረተ ልማቶች ዘላቂነት ለማስቀጠልና የዲጂታል ሥነ-ምህዳሩን ደኅንነት ለማረጋገጥ ከፍትሕ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መሥራት ወሳኝ በመሆኑ የተዘጋጀ ነው።
ሥልጠናው በዋናነት በዲጂታል ፋይናንስና በቴሌኮም ዘርፍ የሚፈጸሙ የማጭበርበር ወንጀሎችን (Telecom & Financial Fraud) ለመከላከል እንዲሁም በቴሌኮም መሠረተ ልማት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን በሕግ አግባብ ለመቆጣጠር በሚቻልባቸው ስልቶች ላይ ያተኮረ ነው።
በሥልጠናው መድረክ ላይ የተሳተፉ የፍትሕ ተቋማት ሀላፊዎችና ባለሞያዎች በበኩላቸው፤ መድረኩ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመረዳትና ተገቢውን የሕግ ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ ግንዛቤ የፈጠረላቸው መሆኑን የገለጹ ሲሆን የቴሌኮም መሠረተ ልማትን እንደ ሀገር ሀብት በመጠበቅና ወንጀሎችን በብቃት በመከላከል ረገድ ከኩባንያችን ጋር በቅንጅት ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ኩባንያችን ተመሳሳይ ሥልጠናዎችን በሌሎች ከተሞችም አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፤ ይህ መድረክ ኩባንያችን ለሀገራዊ የዲጂታል መሠረተ ልማት መስፋፋት ከሚያደርገው ጥረት ባሻገር፣ ከቁልፍ የፍትሕ ባለድርሻ አካላት ጋር የላቀ አጋርነት በመፍጠር የዲጂታል ኢኮኖሚው ደኅንነቱ የተረጋገጠ እንዲሆን የሚያስችል መሆኑ ይታመናል።

4 days ago