Logo
Getu Temesgen
ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ እና ፋሜ ባይ ሺራዝ የሀገርን ገጽታ በጥቅል ለማስተዋወቅ በጋራ ለመስራት ተስማሙ
#ethiopia | የፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በዲጂታል ሚዲያና ብራንድ ማስተዋወቅ ላይ የሚንቀሳቀሰው ፋሜ ባይ ሺራዝ የተሰኘው ተቋም የሀገርን ገጽታ የመገንባት ስራ ላይ በትብብር ለመስራት መስማማታቸውን በጋራ ገለጹ።

የዚሁ ዓለም አቀፍ ተቋም መስራች የሆኑት ሺራዝ ሀሰን እና የስራ ባልደረቦቻቸው በፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ ተገኝተው የስራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን፣ ከዚሁ ጎን ለጎንም ከሚዲያው የማኔጅመንት አመራሮች ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ዘርፎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ወቅት ሁለቱም ተቋማት ያላቸውን ልምድና የዲጂታል ሚዲያ አቅም በማስተባበር፣ በሀገር ገጽታ ግንባታ ስራዎች ላይ ተቀናጅተው ለመስራት የሚያስችላቸው ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ይህ ትብብር የሀገርን ገጽታ የማስተዋወቅ ተግባራትን በዘመናዊና ስልታዊ በሆኑ የዲጂታል መንገዶች በተደራጀ መልኩ ለመደገፍ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ ከቱሪዝም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
#digitalmedia #brandpromotion #tourismethiopia #mediapartnership #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.