(ዘ-ሐበሻ ዜና ዳሰሳ) የዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በትናንትናው ዕለት በካይሮ አጭር የጥቂት ሰዓታት ቆይታ በማድረግ፣ ከግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ ጋር በቤተ-መንግስት የምሳ ግብዣ ላይ መወያየታቸውን በዘ-ሐበሻ ዜና መዘገባችን ይታወሳል። የግብፅ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት እንደገለጸው፣ መሪዎቹ በአረብ ሀገራት ደህንነት፣ ጥቅምና በሁለትዮሽ የወዳጅነት ትብብሮች ዙሪያ መክረዋል። ከዚህ አጭር ቆይታ በኋላም ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በፓሪስ በሚካሄደው የቡድን 7 (G7) ሀገራት ጉባኤ ላይ ለመካፈል ወደ ፈረንሳይ ያቀኑ ሲሆን፣ የግብፁ ፕሬዝዳንትም እሳቸውን ተከትለው በዚሁ ስብሰባ ላይ ለመገኘት ወደ ፓሪስ በረዋል።
ይህ የካይሮ አጭር ቆይታ እና የምሳ ግብዣ ከላይ ከላይ ሲታይ የተለመደ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ቢመስልም፣ በጂኦ-ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መነጽር በጥልቀት ሲፈተሽ ግን ከባድ ስሌቶችን ያዘለ ሆኖ እናገኘዋለን።
ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ለግብፅ ተራ ዲፕሎማት ወይም አቻ መሪ ብቻ አይደሉም፤ የግብፅ ኢኮኖሚ ዋነኛ አዳኝ ጭምር ናቸው። ግብፅ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ በዋጋ ግሽበት እና በዕዳ ጫና ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወቅት፣ ዩኤኢ በቅርቡ በ 'ራስ ኤል ሄክማ' የባህር ዳርቻ ልማት ስም ያፈሰሰችው 35 ቢሊዮን ዶላር የሲሲን መንግስት ከከፋ የኢኮኖሚ ውድቀት ታድጎታል። በመሆኑም ይህ የምሳ ግብዣ ግብፅ ለትልቁ የፋይናንስ ደጋፊዋ (አበዳሪዋ) የምታሳየው የክብር እና የስትራቴጂካዊ ታማኝነት ማረጋገጫ ነው።
ሁለቱ መሪዎች ወደ ፓሪሱ የG7 ጉባኤ ከመሄዳቸው በፊት ካይሮ ላይ መገናኘታቸው ድንገተኛ አይደለም። ምዕራባውያን (G7 ሀገራት) በመካከለኛው ምስራቅ ባለው ቀውስ [በተለይም በጋዛው ጦርነት እና በቀይ ባህር የንግድ መስመር የጸጥታ ስጋት] የአረብ ሀገራትን እገዛ አጥብቀው ይፈልጋሉ። ሲሲ እና ቢን ዛይድ ወደ ፓሪስ የያቀኑት "የአረብን ደህንነት በጋራ ለመጠበቅ" በሚል አንድ ወጥ አቋም ይዘው፣ ከምዕራባውያን ሀብታም ሀገራት ጋር የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ድርድር ለማድረግ ነው። አሜሪካ እና አውሮፓ የግብፅን ጂኦግራፊያዊ ድንበር እና የዩኤኢን የፋይናንስ ጡንቻ እንደሚፈልጉት ሁለቱም መሪዎች በሚገባ ያውቁታል።
በተለይም በሱዳን ባለው የእርስ በእርስ ጦርነት ሁለቱ ሀገራት የተለያየ የድጋፍ መስመር እንዳላቸው በስፋት ይነገራል (ግብፅ ለሱዳን ብሄራዊ ጦር፣ ዩኤኢ ደግሞ ለፈጣኖ ደራሽ ኃይሉ - RSF እንደሚያደሉ ይገለጻል)። በመሆኑም ይህ የካይሮ ውይይት በመካከላቸው ሊኖር የሚችለውን የጂኦ-ፖለቲካዊ ልዩነት አጥቦ፣ በምዕራባውያን ፊት ጠንካራ፣ የተግባባ እና የተዋሃደ የአረብ ኃይል ሆነው ለመቅረብ የተደረገ ስልታዊ የቅድመ-ጉባኤ ዝግጅት ነው።
የካይሮው የምሳ ግብዣ የሆድ ሳይሆን፣ የኢኮኖሚ ህልውና እና በምዕራባውያን ፊት የኃይል ሚዛንን የማሳየት ፖለቲካዊ ዝግጅት ነው። ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ ግዙፍ የፋይናንስ ደጋፊያቸውን በማስተናገድ ፖለቲካዊ ክብደታቸውን ሲያሳድጉ፣ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ደግሞ የመካከለኛው ምስራቅ ቁልፍ ደላላ (Power Broker) መሆናቸውን ይዘው ፓሪስ ተገኝተዋል።

2 months ago