Logo
SeledaPost
በአዲስ አበባ ከተማ ፍቃዳቸውን ያላደሱ የጤና ተቋማት ከመስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም በኋላ አገልግሎት መስጠት አይችሉም ተባለ‼️
 
የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በ2019 በጀት ዓመት የጤና ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ እድሳትን በወቅቱ እንዲያጠናቅቁ ጥሪ አቅርቧል።ከ4 ሺህ በላይ የመንግሥትና የግል የጤና ተቋማት እድሳታቸውን ከሐምሌ 1 እስከ ነሐሴ 30 ቀን ድረስ በኦንላይን ሥርዓት ማጠናቀቅ እንደሚገባቸው ባለስልጣኑ አሳስቧል።
 
በአዲስ አበባ ምግብ እና መድኃኒት ባለስልጣን የጤና ተቋማትና ጤና ባለሙያዎች ብቃት ማረጋገጥ ዳይሬክተር አቶ ታደሰ ወርዶፋ ለብስራት ሬድዮ እንደገለጹት ከነሐሴ 30 እስከ መስከረም 30 ቀን ድረስ  ፍቃዳቸውን ያላደሱ ተቋማት በቅጣት ማደስ ይችላሉ። ከመስከረም 30 በኋላ ግን የብቃት ማረጋገጫቸው ወይም የሥራ ፍቃዳቸው ተሰርዞ አገልግሎት መስጠት እንደማችሉ ገልፀዋል።
 
በተጨማሪም ተቋማቱ የጤና ባለሙያዎች ሲቀጠሩ ወይም ሥራ ሲለቁ ለባለሥልጣኑ በወቅቱ ማሳወቅ እንደሚገባቸው ተጠቁሟል።ከ2 ዓመት በላይ ከሙያ ውጪ የነበሩ ባለሙያዎች የሙያ ፍቃዳቸውን ሳያስተካክሉ መቅጠር እንደማይገባ አንስተዋል።
 
Seledadotio
Seledadotio
2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.