Logo
FastMereja
12 ዓመታት የፈጀው የድምፃዊት ፅላት ገዝሙ አልበም ሊወጣ ነው።

​#fastmereja I ድምፃዊት ፅላት ገዝሙ ረጅም ዓመታትን የፈጀውን እና 10 ሙዚቃዎችን የያዘውን "ስኬት" የተሰኘ አዲስ አልበሟን ሰኔ 12/2018 ዓ.ም ለህዝብ ይፋ እንደምታደርግ አስታወቀች።

አልበሙ በዕለቱ በራሷ የዩቲዩብ ቻናል እና በዞጃክ ዎርልድ ዋይድ (Zojak Worldwide) አማካኝነት በመላው ዓለም በአንድነት ይለቀቃል።

​አርቲስቷ ለአልበሙ መውጣት ከ12 ዓመታት በላይ ዝግጅት ስታደርግ የቆየች ሲሆን፣ በውስጡም የተካተቱት 10 ስራዎች የጥበብ አስተዋጽኦዋን ወደ ሌላ ከፍታ የሚያሳድጉ እንደሆኑ ተገልጿል።

በተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቋንቋዎች በመዝፈን ተወዳጅነትን ያተረፈችው ፅላት፣ የ2018 ዓ.ም የኦዳ አዋርድ አሸናፊ መሆኗ ይታወቃል።

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.