በአማራጭ የህፃናት እንክብካቤ ላደጉ ወጣቶች የተዘጋጀዉ የመጀመሪያው የስፖርት ፌስቲቫል ተጠናቀቀ!
#fastmereja I በአማራጭ የህፃናት እንክብካቤና ማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ አድገው ለወጡ ወጣቶች የተዘጋጀው እና ላለፉት ሁለት ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው የመጀመሪያው የስፖርት ፌስቲቫል የፍፃሜ ውድድር በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ በድምቀት ተጠናቋል።
ይህ የስፖርት ፌስቲቫል የተዘጋጀው ወጣቶቹ ከነበሩባቸው የማሳደጊያ ተቋማት ከወጡ በኋላ የሚገጥሟቸውን ዘርፈ-ብዙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች በጋራ ለመጋፈጥ ባቋቋሙት ብሔራዊ ጥምረት አማካኝነት ሲሆን፣ መርሃ-ግብሩም በዴንማርክ መንግስት የሚደገፈዉ የ"Leave No Youth Behind" (ማንንም ወጣት ወደኋላ አንተዉም) ፕሮጀክት አካል መሆኑ ታዉቋል።
የብሔራዊ አማራጭ የህፃናት እንክብካቤ አድገው የወጡ ወጣቶች ማህበር ጥምረት የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሀላፊ አቶ ምስክር ታደሰ እንደገለጹት፤ የዚህ ስፖርታዊ ውድድር ዋና ዓላማ ወጣቶቹ እርስ በርስ እንዲገናኙ፣ ጤናቸውን እንዲጠብቁ እና ትስስራቸውን ይበልጥ እንዲያጠናክሩ ለማድረግ መሆኑን ገልፀዋል።
በተጨማሪም ወጣቶች ከማሳደጊያ ተቋማት ከወጡ በኋላ የሚያጋጥሟቸውን እንደ ስራ አጥነት እና የመኖሪያ ቤት ችግር ያሉ ፈተናዎችን በጋራ ለመፍታት እንዲሁም ወጣቶቹ እርስ በርስ ጠንካራ ትስስር(Network) እንዲፈጥሩ እና ወደፊት በጋራ ለሚቆሙላቸው መብቶች፣ የፖሊሲ ተፅዕኖ ማሳደርን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ትልቅ መድረክ መፍጠሩን አቶ ምስክር አክለው አብራርተዋል።
በወንዶች የእግር ኳስ እና በሴቶች የመረብ ኳስ (ቮሊቦል) ውድድሮች በተካሄዱበት በዚህ ፌስቲቫል ላይ በርካታ የወጣቶች ማህበራት የተሳተፉ ሲሆን፤ የዓለም አካባቢ ጥበቃ ቀንን በማስመልከትም በዕለቱ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተከናውኗል።
በፌስቲቫሉ ላይ የኤስ ኦ ኤስ (SOS) ህፃናት መንደር ወጣቶችን ያቀፈው “አልሙናይ ዩዝ አሶሴሽን'፣ የሰላም የህፃናት መንደር ወጣቶች ማህበር(ሰላም ፍሩትስ)፣ እንዲሁም እንደ ኮልፌ፣ ክበበ ፀሀይ እና ቀጨኔ ካሉ የመንግስት ማሳደጊያ ተቋማት የወጡ ወጣቶች የመሰረቱት “ፎር ኬ ኬር ሊቨርስ ቻሪቲ አሶሴሽን' የተሳተፉ ሲሆን፤ የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ደግሞ በክብር ተጋባዥነት ተገኝቷል።
በኢትዮጵያ የኤስ ኦ ኤስ (SOS) ህጻናት መንደሮች የአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር አቶ አለም ጌታቸው በበኩላቸው፤ ተቋማቸው ለዚህ የወጣቶች ጥምረት መመስረትና ለፌስቲቫሉ መሳካት የፋይናንስ እንዲሁም የቴክኒክ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።
ድጋፉ በዴንማርክ መንግስት የገንዘብ እገዛ በሚተገበረው ሊቭ ኖ ዩዝ ቢሀይንድ(Leave No Youth Behind) ፕሮጀክት አማካኝነት የተደረገ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም ወጣቶቹ ተነቃቅተው ለራሳቸው መብት እንዲቆሙና የፖሊሲ ተፅዕኖ መፍጠር እንዲችሉ ማገዝ እንደሆነ አስረድተዋል።
በመሆኑም ይህንን መሰል የስፖርት መርሃ-ግብሮችን በየወሩ እንዲያካሂዱ፣ በፌስቲቫል ደረጃ ደግሞ በየስድስት ወሩ ወይም ባልተቻለ ሁኔታ በዓመት አንድ ጊዜ በቋሚነት እንዲያዘጋጁ ተቋማቸው ሁለንተናዊ እገዛ ማድረጉን እንደሚቀጥልበት አረጋግጠዋል።

8 hours ago