Logo
Getu Temesgen
ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2027 የሚካሄደውን የዓለም አቀፍ የፀረ-ዶፒንግ ትምህርት ጉባኤን እንድታስተናግድ በይፋ ተመረጠች
#ethiopia | ሀገራችን ኢትዮጵያ ለስፖርቱ ዘርፍ ዕድገት ለሰጠችው ልዩ ትኩረት ትልቅ ማሳያ የሚሆንና ከፍተኛ ፋይዳ ያለው ዓለም አቀፍ የባህልና የስፖርት ኩነትን የማዘጋጀት ዕድል አግኝታለች።

በዓለም አቀፉ የፀረ-ዶፒንግ ኤጀንሲ አስተናጋጅነት በየወቅቱ የሚካሄደው የዓለም አቀፍ የፀረ-ዶፒንግ ትምህርትና ሥልጠና ጉባኤ በፈረንጆቹ 2027 በኢትዮጵያ እንዲሰናዳ ተወስኗል።

ይህ ትልቅ መድረክ በፀረ-አበረታች ቅመሞች እንቅስቃሴ ላይ ሰፊ ተፅዕኖ ያለው ሲሆን ቀደም ሲል እ.ኤ.አ በ2018 በቻይና ቤጂንግ፣ በ2022 በአውስትራሊያ ሲድኒ እንዲሁም በ2024 በፈረንሳይ ፓሪስ መካሄዱ ይታወሳል።

ይህ የዓለም አቀፍ የፀረ-ዶፒንግ ትምህርት ጉባኤ በአፍሪካ አህጉር ሲካሄድ የአሁኑ የመጀመሪያው ነው። በመሆኑም መድረኩ ለሀገራችን መልካም ገጽታ ግንባታና ለስፖርት ቱሪዝም ዕድገት ከሚያበረክተው ዘርፈ ብዙ ጥቅም ባለፈ በአህጉር ደረጃ ንጹህ ስፖርትን ለማስፋፋትና የፀረ-አበረታች ቅመሞች ቁጥጥርን ይበልጥ ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

ከምንም በላይ ደግሞ ኢትዮጵያ የአበረታች ቅመሞች ወይም የዶፒንግ መከላከል ሥራዎችን በመደበኛው የትምህርት ሥርዓት ውስጥ በማካተት፣ ጠንካራ የሕግ ማዕቀፎችን በማውጣት፣ እንዲሁም አስተማማኝ የምርመራና የቁጥጥር ሥርዓቶችን በመዘርጋት ረገድ ያስመዘገበቻቸውን በርካታ ስኬቶች ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተግባር ለማሳየትና ለማስተዋወቅ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።
#wada #globaleducationconference #cleansport #antidoping #sportstourism #africasports #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

4 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.