መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በመላ ኢትዮጵያ ሊስፋፋ የሚገባው ተሞክሮ ነው
***************
አዲስ አበባ 8ኛውን አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎት ማዕከል ወደ ሥራ
አስገብታለች።
ማዕከሉ በርካታ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ጣሪያ ሥር በማሰባሰብ፣ ዜጎችን የሚያማርሩ የእጅ መንሻ እና አሰልቺ የቢሮክራሲ ሒደቶችን አስቀርቷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በማስፋፋት ረገድ ያከናወነው ሥራም ሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞችና የክልል መስተዳድሮች ልምድ የሚሆን አርዓያነት ያለው ተግባር ነው።
በተለያዩ ክልሎችን ከተሞች መሰል የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎች ቢቋቋሙም አሁንም ይበልጥ ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑ አያጠያይቅም።
መሰል የዲጂታል ማዕከላት በየክልሉ መስፋፋታቸው፣ ወጥና ቀልጣፋ የአገልግሎት ሥርዓት እንዲዘረጋ በማድረግና ቅልጥፍናን በመጨመር የዜጎችን የእንግልት ለመቀነስ ያስችላል።
በመሆኑም የአዲስ መሶብን ተሞክሮ በመላ ኢትዮጵያ በማስፋት፣ ዜጎች ካለእንግልትና ከሙስና በጸዳ መልኩ ተገቢውን አገልግሎት የሚያገኙበትን ሥርዓት መዘርጋት ወቅቱ የሚጠይቀው ተግባር ነው።
#ebc #mesob #modern #service #addisababa

6 hours ago