ዲያስፓራ አዳባባይ መገናኛ አካባቢ በደረሰዉ የተሽከርካሪ አደጋ ምክንያት አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ ፖሊስ አሳሰበ!
ዲያስፓራ አዳባባይ መገናኛ አካባቢ በደረሰዉ የተሽከርካሪ አደጋ ምክንያት አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳሰበ፡፡በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የየካ ክፍለ ከተማ የትራፊክ ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጋሻ ሁነኝ ሙሉጌታ ለኤኤምኤን ዲጂታል እንደተናገሩት አደጋዉ 10፡30 አካባቢ በዲያስፓራ አዳባባይ በታክሲ ተርሚናሉ አካባቢ የደረሰ ሲሆን በአደጋዉ ሁለት ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዉ በህክምና ላይ ይገኛሉ፡፡
በታክሲ ተርሚናሉ ዉስጥ በተለምዶ ቅጥቅጥ የሚባለዉ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ወደ ኋላ ሲያሽከረክር ወድቆ ተንጠልጥሎ እንደሚገኝ ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡ተሽከርካሪዉ በአሁኑ ወቅት ከላይኛዉ ትሚናል ወደ ታችኛዉ ተርሚናል ተንጠልጥሎ ይገኛል፡፡የእሳትና አደጋ መከላከል አሽከርካሪዎች በቦታዉ ደርሰዉ ተሽከርካሪዉን ለማንሳት ጥረት እያደረጉ መሆኑን የገለጹት ሃላፊዉ ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ክትትል እየተደረገ ይገኛል፡፡
ከቀበና መጥተዉ ወደ ኮተቤ የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች በሚናሮል ጀርባ በኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ባለዉ አማራጭ መንገድ እንዲጠቀሙ አሳስበዋል፡፡የትራፊክ ፖሊሶች በአካባቢዉ የትራፊክ እንቅስቃሴዉን በማሳላጥ ላይ እንደሚገኙም የየካ ክፍለ ከተማ የትራፊክ ዲቪዥን ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጋሻ ሁነኝ ሙሉጌታ ለኤኤምኤን ዲጂታልተናግረዋል፡፡
Seledadotio

8 hours ago