"በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩን እና ፖሊሲዎቻቸውን ይደግፋሉ። እንዲሁም በምንም ዓይነት ምክንያት ፖሊሲዎቻቸውን የሚቃወሙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች አሉ። ነገር ግን ይህ የተለየ ምርጫ፣ እኔ እስከምረዳው ድረስ፣ የእርሳቸው ተወዳጅነት ምን ያህል እንደሆነ የሚፈትሽ ብቻ ሳይሆን፣ ሰዎች በየቦታው ባለው አነስተኛ ግጭት እና ሁከት ምን ያህል እንደተማረሩ የሚያሳይ ነው።
"ሰሞኑን ጅማ ነበርኩ... አሁን ደግሞ አዲስ አበባ ነኝ፣ ቢያንስ በጅማ እና አዲስ አበባ ምርጫ ሲካሄድ አይቻለሁ። ሰዎች በነቂስ ወጥተው ድምጽ ይሰጡ ነበር። በአንዳንድ አካባቢዎች የተወሰኑ የተቃዋሚ ኃይሎች የጦር መሣሪያዎችን እና ፈንጂዎችን ጭምር በመጠቀም ድምጽ አሰጣጡን ለማስቆም መሞከራቸውን አውቃለሁ። ነገር ግን በሺዎች፣ አልፎ ተርፎም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የዚህን ዓይነት ሙከራዎች ተቋቁመው ድምጻቸውን ለመስጠት ሲወጡ አውቃለሁ።
"እናም ጠቅላይ ሚኒስትሩንና ፖሊሲዎቻቸውን የሚደግፉ እና በዚህም መሠረት ድምጽ የሚሰጡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ፣ ሌሎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የጠቅላይ ሚኒስትሩን ወይም የገዥውን ፓርቲ ፖሊሲዎች ቢቃወሙም፣ በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተስፋፋ በመጣው የሁከት ድርጊት የተጸየፉ እንደሆኑ ለማመን የሚያስችል ምክንያት አለኝ። ስለዚህ ምርጫው የርሳቸውን ፖሊሲዎች እንደመደገፍ ሁሉ፣ ሁከትንም የመቃወም ጉዳይ ነበር።"
ጌታቸው ረዳ ለቱርኩ ቲአርቲ ከሰጡት ቃለምልልስ

2 months ago